የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23 ጀምሮ ተማሪዎችን ይቀበላሉ
ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን የሚቀበሉበት የጊዜ መርሃ ግብር በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚ/ር ወጥቷል
በመጀመሪያ ዙር ተመራቂ ተማሪዎች ይገባሉ
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23 ጀምሮ ተማሪዎችን ይቀበላሉ
በ2012 ዓ.ም በኮቪድ-19 ወረርሽን ምክንያት የተቋረጠውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር እና የ2013 የትምህርት ዘመን እንዲቀጥል መንግስት መወሰኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ዩኒቨርሲቲዎች በመጀመሪያ ዙር ተመራቂ ተማሪዎችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ይሁንና ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉንም ተመራቂ ተማሪዎች በተመሳሳይ ቀናት የሚጠሩና የሚቀበሉ ከሆነ ካለው የትራንስፖርት እጥረት አንፃር ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ የመጋለጥ ሁኔታ የሚጨምር ስለሆነ የተቋማት የቅበላ መርሃ ግብር እንደ ማዕከል ወጥቷል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
1. ጥቅምት 23 እና 24 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ
ሐዋሳ ዩኒቨርስቲ
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ
መቐለ ዩኒቨርስቲ
ራያ ዩኒቨርስቲ
ወሎ ዩኒቨርስቲ
መቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ
ሠመራ ዩኒቨርስቲ
2. ጥቅምት 25 እና 26 ቀን 2013 ዓ.ም
አርሲ ዩኒቨርስቲ
ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ
ሰላሌ ዩኒቨርስቲ
ደብረ ብረሃን ዩኒቨርስቲ
ዲላ ዩኒቨርስቲ
መዳወላቡ ዩኒቨርስቲ
አክሱም ዩኒቨርስቲ
አዲግራት ዩኒቨርስቲ
ወልዲያ ዩኒቨርስቲ
አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ
ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ
ጂንካ ዩኒቨርስቲ
አምቦ ዩኒቨርስቲ
3. ጥቅምት 27 እና 28 ቀን 2013 ዓ.ም
ጅማ ዩኒቨርስቲ
ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ
ቦንጋ ዩኒቨርስቲ
ሐረማያ ዩኒቨርስቲ
ኦዳቡልቱም ዩኒቨርስቲ
ቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ
ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ
ደባርቅ ዩኒቨርስቲ
እንጂባራ ዩኒቨርስቲ
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ
ወራቤ ዩኒቨርስቲ
4. ጥቅምት 29 እና 30 ቀን 2013 ዓ.ም
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ
መቱ ዩኒቨርስቲ
ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ
ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ
ጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ
ወለጋ ዩኒቨርስቲ
ደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ
አሶሳ ዩኒቨርስቲ
5. ከጥቅምት 28 እስከ 30 ቀን 2013 ዓም
ጎንደር ዩኒቨርስቲ
ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ
ደብረታቦር ዩኒቨርስቲ