
የትግራይ ክልል እና የመተከል ዞን ተማሪዎች በልዩ የውጤት ሁኔታ ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ተወስኗል
የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መሰረት በተፈጥሮ ሳይንስ ለወንድ 380 ሲሆን ለሴት ደግሞ 368 ሆኗል፡፡
ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ለወንድ 370 ሲሆን ለሴት 358 መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ለታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ለወንድ 368 ለሴት 358 ነው ተብሏል፡፡
ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ለወንድ 358 ሲሆን ለሴት 348 መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡
የትግራይ ክልል እና የመተከል ዞን ተማሪዎች ደግሞ በልዩ የውጤት ሁኔታ ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ የተወሰነ ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 358 ሴት 350፤ በማህበራዊ ሳይንስ ወንድ 348 ሴት 340 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲዎች እንደሚገቡ ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን 147 ሺ 640 ተማሪዎች ወደ 46 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እንደሚገቡ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡