ከ22ቱ 8ቱ የሳዑዲ አውሮፕላኖች ናቸው
ሳዑዲን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት አውሮፕላኖች በኢትዮጵያ እየተጠገኑ ነው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጭነትና በአውሮፕላን ጥገና ዘርፎች የተሻለ አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡
ከኢቲቪ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአየር መንገዱ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በአሁኑ ወቅት ለተለያዩ ሃገራት አየር መንገዶች የጥገና ግልጋሎቶችን እየሰጠን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ለዚህም አገልግሎቱን ያገኙ የሳዑዲ አረቢያ አየርመንገድንና የሌሎችንም ሃገራት አውሮፕላኖች በምሳሌነት አንስተዋል፡፡
አል ዐይን አማርኛ ከአየር መንገዱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል እንዳገኘው መረጃ ከሆነ ከጥቂት ወራት በፊት አራት የሳዑዲ አውሮፕላኖች ተጠግነው ወጥተዋል፡፡
ባለፉት ሶስት ወራትም 8 የሳዑዲ፣ 3 የርዋንዳ፣ 2 የሪዩኒዬን ደሴቶች፣ 3 የናይጄሪያ፣ 4 የቶጎ እና 2 የማላዊ በድምሩ 22 አውሮፕላኖችም በአየር መንገዱ ተጠግነዋል፡፡