የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በምን ጉዳዮች ላይ ተወያዩ?
በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ ሰሞኑን በሞስኮ ቆይታ አድርጓል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ በሞስኩ ውይይቶችን ያደረገ ሲሆን ስምንነትም ተፈራርሟል
በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ጳጳስ የተመራው የኡትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልዑካን ቡድን ሰሞኑን በሞስኮ ቆይታ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ በሞስኩ ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር መወያየቱን የሞስኮ መንበረ ፓትርያርክ ጽሕፈት ቤት ዘግቧል።
ልኡኩ ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ በአፍሪካ የሩሲያ ቤተ ክርስቲያን የበላይ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሊዮኒድ እንዲሁም ሌሎች ልዑካን ጋር ውይይት ማድጉ ተነግሯል።
በውይይቱ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ የሩሲያ ቤተ ክርስቲያን ያለችበት ቀውስ ከኢትዮጵያ ጋር ይመሳሰላል ብለዋል።
ውጫዊ ግፊት ባለበት ሁኔታ ቤተ ክርስቲያኗን በዘር ለመክፈል የተደረገው ሙከራ ቤተ ክርስቲያኗን ጎድቷል ያሉት ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ የሩሲያ ቤተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጎን ናት ሲሉ ገልጸዋል።
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በበኩላቸው በታሪክ አስቸጋሪ በተባለው ክስተት ወቅት የሩሲያ ቤተ ክርስቲያን ከጎናችን በመቆሟ እናመሰግናለን ብለዋል። የሩሲያ እና የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት በቦታ የሚራራቁ ቢሆንም በመንፈስ አንድ ናቸው ብለዋል።
በስብሰባው መጨረሻ ላይ የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች የሁለትዮሽ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ስምምነቱም ወደ ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ፓትርያርኮች ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር በማውገዝ ለቅዱስ ሲኖዶስ ድጋፍ መግለጻቸው ይታወሳል።
ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ በመልክታው፤ ምድራዊ ፍርሃትን የሚቃወሙት ኦርቶዶክሳዊያን ጥንካሬ ለመጪው ትውልድ ምሳሌ እንደሚሆን አምናለሁ” ብለዋል።