መንግስት ስለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ባወጣው መግለጫ ሰልፍ እንዳይደረግ ከለከለ
መንግስት "ህገወጥ የሰልፍ ጥሪዎች" ለማድረግ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው ብሏል
በመንግስት በኩል ከተወገዙት አካለት ጋር በአቻ መታየቷንም ቤተክርስቲያኗ መቃወሟ ይታወሳል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን ሁኔታ መገምገሙን የገለጸው የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ባወጣው መግለጫ "ህገወጥ የሰልፍ ጥሪዎች" ለማድረግ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው ብሏል።
ግብረኃይሉ "በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ" የሰልፍ ጥሪ በማድረግ ግጭት የሚቀሰቅሱ ተግባራት እየተፈጸሙ መሆኑን ገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በተለየ የምንደግፈው፤ በተለየ የምንቃወመው ኃይል የለም” ሲሉ ስለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተናገሩ
ቤተክርስቲያኗ ካወገዘቻቸው "ቡድኖች" ጋር እኩል መታየቷን ተቃወመች
መግለጫው "በሀይማኖት ሽፋን" የተጠራው ሰልፍ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ ለማስተጓጎል ያለመ ነው ብሏል።
ማሳሰቢያውን በመተላለፍ ሰልፍ ለማድረግ በሚንቀሳቀስ አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ግብረ ኃይሉ አስጥቅቋል።
የውጭ ኃይሎች "በቅርቡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ እድል በመጠቀም" ችግሩን ለማባባስ እየተንቀሳቀሱ ነው ብሏል መግለጫው።
ከሁለት ሳምንታት በፊት ሶስት የሀይማኖት አባቶች በደቡብ ምዕራብ ሽዋ ሀገረ ስብከት የኢጲስ ቆጶሳት ሲመት ማካሄዳቸውን ተከትሎ ነበር በቤተክርስቲያኗ ችግር የተፈጠረው።
ይህን ተከትሎ የቤተክርስቲያ ቅዱስ ሲኖዶስ ከቀኖና ስርአተ ቤተክርስቲያን ውጭ ሲመት የሰጡትንና የተቀበሉትን ከቤተክርስቲያኗ እንዲለዩ፣ እንዲወገዙ እንዲሁም ስልጣነ ክህነታቸው ከድቁና ጀምሮ ያለው እንዲነሳ መወሰኑ ይታወሳል።
ቤተክርስቲያ ያወገዘቻቸው "ቡድኖች" በተለይም በኦሮሚያ ክልል በመንቀሳቀስ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በመታገዝ ቤተክርሰቲያን ውስጥ የመግባት ድርጊት እየፈጸሙ ነው ስትል ቤተክርስቲየኗ መንግስትን እየተቸች ነው።
በተለይም በኦሮሚያ ክልል ምእመናን ድብደባ እና ግድያ እየደረሰባቸው መሆኑን የገለጸችው ቤተክርስቲያኗ፣ መንግስት ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲያስከብርላት እየጠየቀች ነው።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤም(ኢሰመጉ) ትናንት ባወጣው መግለጫ በቤተ-ክርስቲያን እውቅና ያልተሰጣቸውን ኤጲስ ቆጶሳት በተለያዩ አብያተ-ክርስቲያናት መመደብ አግባብ አይደለም በማለት የተቃወሙ አማኞች በተለይም በኦሮሚያ ክልል የመብት ጥሰት ገጥሟቸዋል ብሏል።
መንግስት የቤተክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ልእልና፣ መብትና ጥቅም የማስከበር ህገመንግስታዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንዲያስከብር ቤተክርስቲያኗ አሳስባለች።
መንግስት በበኩሉ ለማንም እንደማይወግን እና ጉዳዩ በውይይት ሊፈታ የሚችል ነው ብሏል።
በመንግስት በኩል ከተወገዙት አካለት ጋር በአቻ መታየቷንም ቤተክርስቲያኗ መቃወሟ ይታወሳል።
ቤተክርስቲያኗ፣ መንግስት ተቋማዊ ልእልናዋን ካላስጠበቀ እና በምእመናን ላይ የሚደርሰው እስርና ወከባ የማይቆም ከሆነ የካቲት 5 ሰልፍ እንደምታደረግ መግለጿ ይታወሳል።