የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ ሩሲያ ገባ
ልዑኩ በሞስኮ ቆይታው ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ጋር ይመክራል
በሁለትዮሽ የአብያተ ክርስቲያናቱ ቀጣይ ግንኙነት ላይ ውይይት እንደሚደረግም ቤተ ክርስቲያኗ አስታውቃለች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ ለሁለትዮሽ ውይይት ሩሲያ መግባቱ ተገለፀ።
በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሞስኮ መግባቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብዙሃን መገናኛ ድርጅት አስታውቋል።
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን መንግስት አቋሜን ተቀብሏል አለች
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከመንግስት ጋር እየተነጋገረች መሆኑን አስታወቀች
ልዑኩ በቆይታው ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ጋር የሚወያይ መሆኑን ዘገባው አመላቷል።
እንዲሁም ልኡኩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መልዕክትን የሚያደርስ ሲሆን፤ በሁለትዮሽ የአብያተ ክርስቲያናቱ ቀጣይ ግንኙነት ላይ ውይይት ውይይት ያደርጋል ተብሏል።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር በማውገዝ ለቅዱስ ሲኖዶስ ድጋፍ መግለጻቸው ይታወሳል።
ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ በመልክታው፤ ምድራዊ ፍርሃትን የሚቃወሙት ኦርቶዶክሳዊያን ጥንካሬ ለመጪው ትውልድ ምሳሌ እንደሚሆን አምናለሁ” ብለዋል።
ከሁለት ሳምንታት በፊት ሶስት የሀይማኖት አባቶች በደቡብ ምዕራብ ሽዋ ሀገረ ስብከት የኢጲስ ቆጶሳት ሲመት ማካሄዳቸውን ተከትሎ ነበር በቤተክርስቲያኗ ችግር የተፈጠረው።
ይህን ተከትሎ የቤተክርስቲያ ቅዱስ ሲኖዶስ ከቀኖና ስርአተ ቤተክርስቲያን ውጭ ሲመት የሰጡትንና የተቀበሉትን ከቤተክርስቲያኗ እንዲለዩ፣ እንዲወገዙ እንዲሁም ስልጣነ ክህነታቸው ከድቁና ጀምሮ ያለው እንዲነሳ መወሰኑ ይታወሳል።
ቤተክርስቲያ ያወገዘቻቸው "ቡድኖች" በተለይም በኦሮሚያ ክልል በመንቀሳቀስ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በመታገዝ ቤተክርሰቲያን ውስጥ የመግባት ድርጊት እየፈጸሙ ነው ስትል ቤተክርስቲየኗ መንግስትን መተቸቷም ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከመንግስት ጋር በተደረገ ውይይት የቤተ-ክርስቲያኒቱን አቋም ቅቡልነት እንዳገኘ ባሳለፈው ቅዳሜ ማሳወቁም ይታወሳል።
መንግስት የቤተ ክርስቲያንን አቋም በመቀበል ወደፊትም የቤተ-ክርስቲያንን አንድነት እና ሉዓላዊነትን በጠበቀ መንገድ እንደሚሠራ ማረጋገጡን ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው አረጋግጧል።