ኢሰመጉ በኦሮሚያ ክልል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ግድያና ድብደባ የፈጸሙ የጸጥታ አካላት እንዲጠየቁ ጥሪ አቀረበ
መንግስት የኃይማኖት ነጻነትንና የዜጎችን ደህንነት እንዲያስከብርም ጥሪ አቅርቧል
ኢሰመጉ ይህን ያለው ከኃይማኖት ጋር ተያይዞ ባለው ወቅታዊ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫ ነው
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በቤተ-ክርስቲያን እውቅና ያልተሰጣቸውን ኤጲስ ቆጶሳት በተለያዩ አብያተ-ክርስቲያናት መመደብ አግባብ አይደለም በማለት የተቃወሙ አማኞች በተለይም በኦሮሚያ ክልል የመብት ጥሰት ገጥሟቸዋል ብሏል።
ለማሳያነት ሻሸመኔ ከተማን የጠቀሰው ኢሰመጉ ከመንግስት የጸጥታ አካላት በተተኮሱ ጥይቶች የሰዎች ህይወት ማለፉንና የአካል ጉዳት መድረሱን አረጋግጫለሁ ሲል ገልጿል።
ጉባኤው ሰበሰብኩት ባለው መረጃ በያቤሎ አካባቢበቤተ-ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ላይ እስራት፣ ማዋከብና ድብደባ መፈጸሙንም አስታውቋል።
በተለያዩ አካባቢዎች ይህንን አካሄድ በተቃወሙ የእምነቱ ተከታዮችና አገልጋዮች ላይ ድብደባዎች፣ ቤት ሰብሮ በመግባትና እስራቶች እየተከናወኑ ነው ብሏል።
ከቅዱስ ሲኖዶስ በተላለፈ መልዕክት መሰረት ጥቁር ልብስ የለበሱ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ እስሮችና ድብደባዎችን መንግስት እንዲያስቆምም ወትውቷል።
ከህግ አግባብ ውጪ ግድያ፣ እስራት፣ ደብደባ እና ሌሎችም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የፈጸሙ የጸጥታ አካላትን መንግስት ተጠያቂ እንዲያደርጋቸው ጉባኤው ጠይቋል።
ኢሰመጉ ኃይማኖት የማህበራዊ መስተጋብር አንዱ ክፍልና መብት በመሆኑ መንግስት የማህበረሰቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣና የዜጎችን ደህንነት እንዲያስከብር ጥሪ አቅርቧል።
ለዚህም የህገ-መንግስቱን አንቀጽ 11ና 27 እንዲሁም ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን የጠቀሰው ኢሰመጉ፤ በእምነቱ ተከታዮች ላይ እየደረሰ ያለው የመብት ጥሰት እንዲቆም ጠይቋል።
"...የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ላይ የሚፈጽሙትን ከህግ አግባብ ውጪ የሆነ ግድያ፣ አካል ማቁሰል፣ ድብደባ እና እስር እንዲያቆም [ኢሰመጉ] ጥሪ ያቀርባል" ብሏል ኢሰመጉ።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን ጋር ተያይዘው የተነሱ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮችን ሲከታተል መቆየቱን ጠቅሶ፤ ሙሉ ምርመራውንም ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ከሁለት ሳምንታት በፊት ሶስት የሀይማኖት አባቶች በአሮሚያ ክልል አንድ ሀገረ ስብከት የኢጺስ ቆጶሳት ሲመት ማካሄዳቸውን ተከትሎ ነበር በቤተክርስቲያኗ ችግር የተፈጠረው።
ይህን ተከትሎ የቤተክርስቲያ ቅዱስ ሲኖዶስ ከቀኖና ስርአተ ቤተክርስቲያን ውጮ ሲመት የሰጡትን እየተቀበሉትን ከቤተክርስቲያን እንዲለዩ፣ እንዲወገዙ እንዲሁም ስልጣ ክህነታቸው እንዲነሳ መወሰኑ ይታወሳል።
ቤተክርስቲያ ያወገዘቻቸው ቡድኖች በተለይም በኦሮሚያ ክልል በመንቀሳቀስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ቤተክርሰቲያን ውስጥ የመግባት ድርጊት እየተፈጸመነው ስትል ቤተክርስቲየኗ መንግስትን እየተቸች ነው።
መንግስት ህግ እንዲያስከብር እየጠየቀች ነው።
መንግስት በበኪሉ ለማንም እንደማይወግን እና ጉዳዩ በውይይት ሊፈታ የሚችል ነው ብሏል።
ቤተክርስቲያኗ መንግስት ግን ካወገዘቻቸው አካለት በአቻ ማየቱ መንግስት ጣልቃ ስለመግባቱ ማሳያ ነው ብላለች።