ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በተለየ የምንደግፈው፤ በተለየ የምንቃወመው ኃይል የለም” ሲሉ ስለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተናገሩ
ቤተክርስቲያኗ ህገወጥ ሹመት ሰጥተዋል ያለቻቸውን አባቶች ማውዟ ይታወሳል
መንግስት የሚቃውመውም ሆነ የሚደግፈው አካል የለም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትናንትናው እለት ከካቢኔያቸው ጋር ባደረጉት ውይይት ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስለተፈጠረው ችግር አስተያየት ስጥተዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት በደቡብ ምእራብ ሽዋ ሀገር ስብከት ሶስት የሀይማኖት አባቶች ለሌሎች 26 ኢጲስ ቆጶሳት ሹመት ሰጥተናል ማለታቸውን ተከትሎ ነበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ ከባድ የተባለ ችግር የተፈጠረው፡፡
- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተፈጠረው ችግር ላይ የመንግስት ምላሽ ምን ይሆናል?
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሶስት የሀይማኖት አባቶችን ማዕረግ አገደች
በዚህ ምክንያት ቤተክርስቲያኗ አስቸኳይ የሲኖዶስ ጉባኤ በመጥራት፤ ከቤተክርስቲያኗ ቀኖና ስርአት ውጭ የኢጲስ ቆጶሳት ሹመት ያደረጉት ሶስት የኃይማኖት አባቶች እንዲወገዙ እና ከቤተክርስቲያን እንዲለዩ መወሰኗ ይታወሳል፡፡
ተወግዘው ከቤተክርስቲያን እንዲለዩ የተደረጉት አባ ሳዊሮስ እና ሹመት የተቀበሉት ሁሉም ከድቁና ጀምሮ ያለው ስልጣነ ክህነታቸው እንዲነሳም ጉባኤው ወስኗል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከካኔያቸው ጋር ባደረጉት ስብሰባ እና በቴሌቪዥን በተላለፈው ስብሰባ በቤተክርስቲያኗ ላይ የተፈጠረው ችግር በሰከነ ሁኔታ ማየት ከተቻለ ሊፈታ የሚችል ቀላል ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
“በጣም ቀላል ነው፡፡ …ከባድ ነው ብየ አልወስድም” ብለዋል
ቤተክርስቲያኗ በሲኖዶሱ የተወሰኑት ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ መንግስት ህግ እንዲያስከብርላት ጠይቃለች፡፡
ነገርግን መንግስት የሚቃውመውም ሆነ የሚደግፈው አካል እንደሌለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል፡፡
“በተለየ የምንደግፈው፤ በተለየ የምንቃወመው ኃይል የለም፡፡ ሁሉም ሃይሎች ኦርቶዶክሶች ናቸው፤ ሁለቱም ጋር ያሉ ጥያቄዎች እውነትነት አላቸው“ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በስክነት ችግሮች መፈታት እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡
የካቤኔ አባላቶችን በጉዳይ ጣልቃእንዳይገቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቀቅዋል፡፡
መንግስት ጣልቃ እንደማይገባ የተናሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እጃቸው ያስገቡ አካላት አሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሲኖዶሱ የተወገዙት አባቶች ከቋንቋ እና ሀብት ክፍፍል ጋር በተያያዘ ችግር እንዳለ እየገለጹ ሲሆን የሲኖዶሱን ውሳኔም እንደማይቀበሉት እየተናሩ ናቸው፡፡
ሲኖዶሱ የቀኖና ጥሰት ፈጸመዋል የተባሉት አባቶች ይቅርታ የሚጠይቁ ከሆነ ቤተክርስቲያኗ እንደምትቀበላቸው መግለጹ ይታወሳል፡፡