ፖለቲካ
በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን የሕልውና አደጋ ለመመከት አመራሩ ከፊት ተሰልፎ ሚናውን እንደሚወጣ የብልጽግና ፓርቲ ገለፀ
የፓርቲው ፐሬዚዳትን ጨምሮ ሁሉም አመራር ከነገ ጀምሮ ወደ ግንባር እንደሚያቀናም አስታውቋል
የፀጥታ ሀይሉ ከነገ ጀምሮ የተለየ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምርም ገልጿል
የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬው እለት ውይይት አድርጓል።
በመሆኑም ይህን የአገር ሕልውና አደጋ በመመከት የኢትዮጵያን ክብርና ሉአላዊነት ለማስከበር አመራሩ ከፊት ተሰልፎ ሚናውን እንደሚወጣ አስታውቋል።
በዚህም የፓርቲው ፐሬዚዳትን ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ሁሉም አመራር ከነገ ጀምሮ ወደ ግንባር በመሄድ እንደሚፋለምም ፓርቲው አስታውቋል።
።ውጊያው ከዚህ የበለጠ ጉዳትና ኪሳራ እንዳያደርስ የፀጥታ ሀይሉ ከነገ ጀምሮ የተለየ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምርም አስታውቋል
ፓርቲው በውይይቱ አክሎም “የኢትዮጵያን ሕልውና የማይፈልጉ የውስጥ ባንዳዎችና የውጭ ሃይሎች በመቀናጀት በኢትዮጵያ ላይ ሁሉን አቀፍ የሕልውና አደጋ ደቅነዋል” ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።
ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ኢትዮጵያ በታሪኳ ጠንካራ ፈተና እየተጋፈጠች መሆኗን ጠቅሶ፤ በዚሀም ኢትዮጵያዊያን አገራቸውን ለመታደግ በአንድነት ቆመው አኩሪ ተጋድሎ እየፈፀሙ ነው ብሏል።