"... ነገርግን በ2:12 ደቂቃ ልዩነት እሰብረዋለሁ ብየ አስቤ አላውቅም"- አትሌት ትግስት
ያለፈውን አመት ውድድር ያሸነፈችው ትግስት 2 ሰአት፣ ከ11 ደቂቃ፣ከ53 ሰከንድ ነው ውድድሩን ያጠናቀቀችው
ትግስት በአሜሪካ ችካጎ በተካሄደ ውድድር በኬንያዊቷ ብርጊድ ኮስጊ በ2:14:04 ሰአት ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን ከ2 ደቂቃ በላይ በማሻሻል ሰብራዋለች
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ ዛሬ በተካሄደው የበርሊን ማራቶን የሴቶችን የአለም ክብረወሰን መስበር ችላለች።
ያለፈውን አመት ውድድር ያሸነፈችው ትግስት 2 ሰአት፣ ከ11 ደቂቃ፣ ከ53 ሰከንድ ነው ውድድሩን ያጠናቀቀችው።
ትግስት በአሜሪካ ችካጎ በተካሄደ ውድድር በኬንያዊቷ ብርጊድ ኮስጊ በ2:14:04 ሰአት ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን ከ2 ደቂቃ በላይ በማሻሻል ሰብራዋለች።
በኦሎምፒክ የሁለት ጊዜ አሸናፊ የሆነው ኤሉድ ኪፕቾጌ በበርሊን የወንዶች ማራቶን በ2:02:42 ሰአት በማስመዝገብ አምስት ጊዜ ማሸነፍ ክብረወሰን ማስመዝገቡን ቢቢሲ ዘግቧል።
ትግስት ያስመዘገበችው ሰአት በበርሊን 13ኛ ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል። አትሌቷ ባለፈው አመት ያሸነፈችበት 2:15:37 በወቅቱ በሰቶች የውድድር ታሪክ ሶስተኛው ፈጣን ሰአት ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።
ትግስት"በጣም ደስተኛ ነኝ" ብላለች።"ክብረወሰን ለመስበር አስብ ነበር፤ ነገርግን በ2:12 ደቂቃ ልዩነት እሰብረዋለሁ ብየ አስቤ አላውቅም" ሰትል አትሌቷ በደስታ ሰሜት ውስጥ ሆና ተናግራለች።
የቀድሞ የ800 ሜትር ሯጭ የሆነችው ትግስት ማራቶን መሮጥ የጀመረችው ባለፈው አመት ሚያዝያ ነበር።