ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ ያሰለጠነቻቸውን ተማሪዎች ልታስመርቅ ነው
ቦንጋ ዩንቨርስቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሊያስመርቅ መሆኑን ገልጿል
ዩንቨርሲቲው በኢትዮጵያ ቡና ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 37 ተማሪዎችን አስመርቃለሁ ብሏል
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ ያሰለጠነቻቸውን ተማሪዎች ልታስመርቅ ነው።
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መጨረሻ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ 37 ተማሪዎችን በቡና ሳይንስ ትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እንደሚያስመርቅ አሳውቋል።
ዩኒቨርሲቲው የቡና ምርት ኢትዮጵያ ትልቁ የውጭ ምንዛሬ የምታገኝበት ምርት በመሆኑ በ2015 ዓ.ም መጨረሻ 37 ተማሪዎችን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ ይመረቃሉ ብሏል።
ኢትዮጵያ ቡናን ለዓለም ካበረከቱ ሀገራት መካከል አንዷ ብትሆንም እስካሁን ድረስ ግን የቡና ሳይንስ ምሁራን እንዳላፈራች ተገልጿል።
የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳሉት የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቡና ሳይንስ ትምህርት ክፍል እራሱን ችሎ በ2012 እንዲከፈት ማድረጉን ተናግረዋል ።
- ኢትዮጵያ በታሪክ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ወደ ውጪ መላኳን ገለጸች
- 10 ሺህ ሲኒ ቡና የተጠጣበት “ታላቁ የቡና ቅመሱ ስነ ስርዓት” አዲስ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዘገበ
በቡና ምርት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመመርመር ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን ቡናን በትምህርትና ምርምር አስደግፎ ለመምራት ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ የቡና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል ማቋቋሙንም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል።
በሚቀጥለው ዓመት በሁለተኛ ዲግሪ በቡና ሳይንስ ተማሪዎች ይመረቃሉ ያሉት ዶክተር ጴጥሮስ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ጊዜትም የቡና ሳይንስ ትምህርት መስክን በዶክትሬት ዲግሪ ደረጃ ማስተማር እንደሚጀምርም አክለዋል።
ዩኒቨርሲቲው ካለው 200 ሄክታር መሬት ውስጥ በ150 ሄክታሩ ላይ የግብርና ምርቶችን እያከናወነ መሆኑን ፕሬዝደንቱ ገልጸዋል።