አርመኖች ከአወዛጋቢው የናጎርኖ ካራባህ ግዛት ሊወጡ መሆኑ ተገለጸ
አዘርባጃን በቅርቡ በወሰደችው ወታደራዊ እርምጃ የአርመን ታጣቂዎች ትጥቅ ለመፍታት እና ተኩስ ለማቆም መስማማታቸውን መግለጿ ይታወሳል
አማካሪው 120ሺ የሚሆኑት የካራባህ አርመኖች የላችን ኮረመደርን መቼ አቋርጠው እንደሚወጡ ግልጹ አላደረጉም
በአወዛጋቢው የናጎርኖ ካራባህ ግዛት የሚኖሩት አርመኖች ለቀው ሊወጡ መሆናቸውን የመሪያቸው አማካሪ ተናግረዋል።
- አዲሱ የናጎርኖ-ካራባህ የተኩስ አቁም ስምምነት በሰዓታት ውስጥ ተጣሰ
- ፕሬዝደንት ኤርዶጋን “ታሪክን በደንብ ተማር” ሲሉ ፕሬዝደንት ባይደን ስለአርመን የተናገሩትን ተቃወሙ
በአዘርባጃን ስር ሆኖ መተዳደር እንዳይፈልጉ እና የብሄር ጥቃት እንደሚደርስባቸው ስጋት የገባቸው የግዛቷ አርመኖች ወደ አርመኒያ እንደሚሄዱ የግዟቷ አመራር መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
"ህዝባችን የአዘርባጃን አካል ሆኖ መኖር አይፈልግም። 99.6 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ወደ ታሪካዊ መሬታችን መሄድን ይመርጣል" ሲሉ ራሱን አርትሳህ ሪፐብሊክ ሲል የሚጠራው ፕሬዝደንት ሳምቬል ሻህራማንያን አማካሪ ዴቪድ ባብያን ተናግረዋል።
አማካሪው 120ሺ የሚሆኑት የካራባህ አርመኖች የላችን ኮረመደርን መቼ አቋርጠው እንደሚወጡ ግልጹ አላደረጉም።
"የህዝባችን እጣፈንታ በታሪክ ለአርመኖች እና ለሰለጠነው አለም አዋራጅ እና አሳፋሪ ይሆናል። ለዚህ ተጠያቂ የሆኑ አካላት አንድ ቀን በሀጢያታቸው በእግዚአብሄር ፊት ተጠያቃ ይሆናሉ" ብለዋል አማካሪው።
አዘርባጃን በቅርቡ በወሰደችው ወታደራዊ እርምጃ የአርመን ታጣቂዎች ትጥቅ ለመፍታት እና ተኩስ ለማቆም መስማማታቸውን መግለጿ ይታወሳል።
ግጭቱን በጽኑ ያወገዙት የተመድ ዋና ጸሀፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም እና በፈረንጆቹ 2020 የተፈረመው ተኩስ አቁም እና አለምአቀፋ የሰብአዊነት ህግ በጥብቅ ሊከበር የሚል ማሳሰቢያ ሰጥተው ነበር።