በአውሮፓ በአየር ብክለት ምክንያት በዓመት 238 ሺህ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
በአውሮፓ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች 96 በመቶ ለብክለት የተጋለጡ ናቸው ተብሏል
የአውሮፓ ህብረት በ2050 የአየር ብክለትን ዜሮ የማድረስ እቅድ ነበረው
በአውሮፓ በአየር ብክለት ምክንያት በዓመት 238 ሺህ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
የአውሮፓ አካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ የአየር ብክለት ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ በ27 ሀገራት ያስጠናውን የጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል።
በዚህ ጥናት መሰረትም በአውሮፓ በፈረንጆቹ 2020 በአየር ንብረት ብክለት ምክንያት በትንሹ 238 ሺህ ሰዎች የለጊዜያቸው ህይወታቸውን አጥተዋል ተብሏል።
ይህ ወቅት የኮሮና ቫይረስ የተከሰተበት እና የአየር ብክለቱ የቀነሰበት ወቅት ቢሆንም የሟቾች ቁጥር ግን በተቃራኒው እንደጨመረ ሮይተርስ የኤጀንሲውን የጥናት ውጤት ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት መካከል ካሉ ነዋሪዎች መካከል 96 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች ለአየር ብክለት የተጋለጡ መሆናቸውንም የዚሁ ተቋም ሪፖርት ያስረዳል።
የአየር ብክለቱ ዜጎችን ያለእድሜያቸው እንዲሞቱ ከማድረጉ ባለፈ ለዘላቂ እና ጽኑ ህመም እየዳረጋቸው እንደሆነ ተገልጿል።
የተሸከርካሪ ምርቶች፣ በየመኖሪያ ቤቱ ጥቅም ላይ የሚውሉ የከሰል ምርቶች ዋነኞቹ አየርን በካዮች ናቸው የተባለ ሲሆን እነዚህ መርዛማ ጋዞች ወደ ሰው ልጆች ዘልቀው በመግባት ለአስም፣ ሳንባ እና ሌሎች የመተንፈሻ አካላት ህመሞችን አድርሰዋል ተብሏል።
በናይትሮጂን ዳይ ኦክሳይድ ጋዝ ምክንያት ብቻ በየዓመቱ 49 ሺህ የአውሮፓዊያን ያለጊዜያቸው ህይወታት ማለፉ ሲገለጽ ቸውን አጥተዋል የተባለ ሲሆን 24 ሺህ ያህሉ ደግሞ በኦዞን መጎዳት መሞታቸው ተገልጿል።
የአውሮፓ ህብረት በፈረንጆቹ 2050 ላይ የአየር ብክለትን ዜሮ የማድረስ እቅድ ያለው ሲሆን አሁን ባለው አፈጻጸም ከቀጠለ ማሳካት የሚቻለው ግማሽ ያህሉን ብቻ ይሆናል ተብሏል።