ሊዮኔል ሜሲ ለ6ተኛ ጊዜ ባላን ዶርን አሸነፈ፡፡
የባርሴሎና እና የአርጀንቲናው አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ ባላንዶርን ለ6ተኛ ጊዜ በማሸነፍ ትላንት ምሽት በፈረንሳይ ሞናኮ በተደረገው ዝግጅት ሽልማቱን ተረክቧል ፡፡
ሜሲ በቅደም ተከተል ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡትን የሊቨርፑሉ እና የኔዘርላንድ ተከላካይ ቪርጂል ቫን ዳይክ እና ፖርቹጋላዊውን ክርስቲያኖ ሮናልዶን በመርታት ነው የ2019 ባላን ዶር አሸናፊ የሆነው፡፡
የ32 ዓመቱ አርጄምቲናዊ የከዋስ ጠቢብ ከዚህ ቀደም እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2009፣ 2010፣2011፣2012 በተከታታይ እና 2015 ነው የአለም ምርጥ ተጫዋችነት ክብርን የተቀዳጀው፡፡
ሜሲ በ2018/19 የውድድር አመት እስካሁን 54 ጎሎችን ለክለቡ አና ለሀገሩ ያስቆጠረ ሲሆን ባርሴሎናን የላሊጋ ዋንጫ አሸናፊ ሲያደርግ ሀገሩ አርጄንቲና ደግሞ በኮፓ አሜሪካ ሶስተኛ ሆና እንድታጠናቅቅ የመሪነት ሚናውን ተወጥቷል፡፡ “በጣም እድለኛ ነኝ፤ በጣም ተባርኪያለሁ፤ ለረዥም ጊዜ በዚሁ እንደምቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ::” ሲል ሜሲ ከሽልማቱ መኋላ ለ ሪፖርተሮች ተናግሯል፡፡
ሴኔጋላዊው የሊቨርፑል የክንፍ ተጫዋች ሳዲዮ ማኔ የ5 ጊዜ የባላን ዶር አሸናፋን ሮናልዶን በመከተል አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምቷል፡፡
በአውሮፓውያኑ 2018 ከረሼያዊው ሉካ ሞድሪች በመካከላቸው ጣልቃ እስከገባበት ጊዜ ድረስ፣ ያለፉትን 10 ዓመታት እየተፈራረቁ የባላን ዶር ክብርን የተቆናጠጡት ሜሲና ሮናልዶ ናቸው፡፡
የዘገባው ምንጫችን ሮይተርስ ነው፡፡