ህብረቱ ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ"ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎች አልተሟሉም" በማለት ታዛቢ የመላክ እቅዱን መሰረዙን አስታውቋል
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ የአውሮፓ ህብረት በምርጫው ጉዳይ እንደማይታዘብ ያስታወቀው፣” የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚዳፈር ስራ ልስራ ብሎ ስላልተፈቀደለት” ነው ብለዋል፡፡
አምባሳደር ዲና እንደገለጹት ህብረቱ ምርጫ ሲታዘብ መጠቀም በሚፈልገው የመረጃ ቴክኖሎጂ እና የምርጫ ውጤት ከምርጫ ቦርድ ቀድሜ ይፋ ላድርግ የሚሉት ፋላጎቶቹ “የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ስለሚፈታተን” ተቀባይነት እንደሌለው ገልጸዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ "ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎች አልተሟሉም" በማለት ታዛቢ የመላክ እቅዱን ሰርዟል፡፡
የህብረቱ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦረል አውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች እንዲልክ በማሰብ ለመጪው የኢትዮጵያ ምርጫ አስፈላጊ ናቸው በተባሉ ቁልፍ መስፈርቶች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከስምምነት ለመድረስ ጥረት ሲያደረግ ቢቆይም አልተቻለም ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ መንግስት በኩል "ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎች አልተሟሉም "፤ ስለዚህም የታዛቢ ልኡክ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊያደርግ የነበረው ስምሪት ተሰርዟል ብለዋል ጆሴፕ ቦረል፡፡
ምርጫ 2013 በመጭው ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ እቅድ አስቀምጧል፡፡