አውሮፓ በ2022 በታሪክ ሁለተኛውን ሞቃት አመት አሳልፋለች
በክብረወሰን የተመዘገበው ከፍተኛ ሙቀት ወንዞችን ከማድረቅና የሰብል ምርታማነትን ከመቀነስ ባሻገር ለሺዎች ህልፈት ምክንያት ሆኗል ተብሏል

የአውሮፓ ህብረት ያወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው፥ በ2022 የተመዘገበው የሙቀት መጠን በ5ኛ ደረጃ ሊቀመጥ ችሏል
አውሮፓ ባለፈው የፈረንጆቹ አመት 2022 በታሪክ ሁለተኛውን ሞቃት አመት ማሰለፏ ተገለጸ።
የአውሮፓ ህብረት ተመራማሪዎች እንዳስታወቁት፥ በ2022 የተመዘገበው የሙቀት መጠን እስካሁን ከተመዘገቡት በ5ኛ ደረጃ ሊቀመጥ የቻለ ነው።
በክብረወሰን የተመዘገበው ከፍተኛ ሙቀት ወንዞችን ከማድረቅና የሰብል ምርታማነትን ከመቀነስ ባሻገር ለሺዎች ህልፈት ምክንያት ሆኗል ተብሏል።
በአውሮፓ ህብረት የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ተቋም (C3S) ከፈረንጆቹ 1950 ጀምሮ የአለምን ሙቀት መመዝገብ ጀምሯል።
በ2022 የተመዘገበው ሙቀት ግን ከ1850 ወዲህ ከታዩ ሞቃታማ አመታት አምስተኛ ደረጃን የሚይዝ ነው ብሏል ተቋሙ።
ያለፉት ስምንት አመታት በተከታታይ የተመዘገበው የሙቀት መጠን ጭማሪ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለመድረሱም የተቋሙ ምክትል ዳይሬክተር ሳማንታ ቡርጌስ ተናግረዋል።
በአውሮፓ ሀገራት በተለይ በጣሊያን፣ ስፔንና ክሮሽያ ባለፈው አመት በክብረወሰንነት የተመገበ ከፍተኛ ሙቀት ያጋጠመ ሲሆን፥ በፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሰፔንና ብሪታንያ ከ20 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች ህልፈት ምክንያት የሆነ የአየር ንብረት ለውጥ ተከስቷል።
የዝናብ እጥረቱ ያስከተለው ድርቅ በአውሮፓ ከ500 አመታት በኋላ ከፍተኛ ሆኖ መመዝገቡም ተነስቷል።የአለም ሙቀትን ለመቆጣጠር የገቡትን ቃልኪዳን አለመፈፀማቸው ዋጋ እያስከፈላቸው ነው።
የአየር ንብረት ለውጡ በተለይ በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ክፉኛ ተጎድተዋል።
በፓኪስታን የደረሰ የጎርፍ አደጋ ብቻ ከ1 ሺህ 700 በላይ ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን የሬውተርስ ዘገባ አስታውሷል።