አውሮፓ የሩሲያን ጥቃት ለመመከት ተጨማሪ 1000 የኑክሌር አረሮች ያስፈልጓታል ተባለ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ለአውሮፓ የሰጡትን የደህነት ዋስትና ያነሳሉ የሚለው ስጋት አውሮፓውያን ከአሜሪካ ነጻ ሆነው ራሳቸውን የሚከላከሉበትን ለመቀየስ እየወያዩ ይገኛሉ

ተመራጩ የጀርመን ቻንስለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ትራምፕ የአውሮፓ እጣፈንታ ብዙም እንደማያስጨንቃቸውና አስተማማኝ የጸጥታ አጋር እንማይሆኑ አስተያየት ተሰጥተዋል
አውሮፓ ቭላድሚር ፑቲን የሚሰነዝሩትን ጥቃት ለመከላከል ተጨማሪ 1000 የኑክሌር አረሮች እንደሚያስፈልጓት የጀርመን የፖለቲካ ሳይንቲስቶች አስጠነቀቁ።
በስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ሁቨር ኢንስቲትዩሽን ቪዚቲንግ ፌሎው የሆነው ዶክተር ማክስሚላን ተርሃሌ ሩሲያ ለማስወንጨፍ ዝግጁ የሆኑ 1500 የረጅም ርቀት ሚሳይሎች ያሏት ሲሆን አውሮፓ ግን ጥቂት መቶዎች ብቻ ናቸው ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ለአውሮፓ የሰጡትን የደህነት ዋስትና ያነሳሉ የሚለው ስጋት አውሮፓውያን ከአሜሪካ ነጻ ሆነው ራሳቸውን የሚከላከሉበትን ለመቀየስ እየወያዩ ይገኛሉ። ተመራጩ የጀርመን ቻንስለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ትራምፕ የአውሮፓ እጣፈንታ ብዙም እንደማያስጨንቃቸውና አስተማማኝ የጸጥታ አጋር እንማይሆኑ አስተያየት ተሰጥተዋል።
የመሀል-ቀኝ ዘመም ክርሰቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ አውሮፓ ከዋሽንግተን ነጻ ሆና ራሷን እንድትከላከል ፈረንሳይና ጀርመን የኑክሌር ትብብራቸውን ማስፋት እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
በጀርመን የአሜሪካ ኑክሌር ጦር መሳሪያዎችን የሚገኙ ሲሆን በኔቶ ኑክሌር መከላከያ ይጠበቃሉ። ነገርግን ትራምፕ ከሩሲያ ጋር እየፈጠሩ ያለው ግንኙነት በበርሊን በተጨማሪ የደህንነት ዋስትና ጉዳይ ውይይት እንዲደረግ ምክንያት ሆኗል።
ፈረንሳይ የኑክሌር ኃይሏ የአውሮፓ መከላከያ ኃይል አካል እንዲሆን የምትፈልግ ሲሆን ዩናይትድ ኪንግደም(ዩኬ) የኑክሌር ፖሊሲ ግን ግልጽ አለመሆኑ ይነገራል።
የእንግሊዙ ጋዜጣ ቴሌግራፍ እንደገለጸው ፈረንሳይ ለሩሲያ ግልጽ መልእክት ለማስተላለፍ ኑክሌር የታጠቁ ተዋጊ ጄቶችን ወደ ጀርመን የመላክ ሀሳብ እንዳላት ይፋ አድርጓል። የፈረንሳይ መንግስት የኑክሌር ዶክትሪኑን አለመቀየሩን ገልጿል።
በጀርመን ከፍተኛ ተደማጭነት ያለው ዶክተር ታርሃሌ ቀደም ሲል አውሮፓውያን 1500 የአሜሪካ የኑክሌር አረሮችን መግዛት ወይም መከራየት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ የዩክሬኑን ጦርነትን ለማስቆም ከሩሲያ ጋር መነጋገራቸውን ተከትሎ የአውሮፓን ደህንነት የሚጎዳ ስምምነት እንዲደረስ ሊያደርጉ ይችላሉ በሚል ዩክሬንና አውሮፓ ስጋት ገብቷቸዋል።