“ያለ ሩሲያ ጋዝና ነዳጅ እንዴት መቀጠል ይቻላል” የሚለው የአውሮፓ ሀገራትን ማሳሰቡ ተገለፀ
የአውሮፓ ህብረት መሪዎች የሩስያ ጋዝ ቅነሳ ዝግጅቶችን ለማሳደግ ተስማምቷል
የአውሮፓ ህብረት “ከዚህ በኋላ ወደ ርካሽ የነዳጅ ዋጋ መመለስ አይታሰብም” ብሏል
የአውሮፓ ህብረት መሪዎች “ያለ ሩሲያ ነዳጅ ህይወት እንዴት መቀጠል አለበት” የሚለው ለይ እቅድ ለማዘጋጀት መስማማታቸው ተገለፀ።
የህብረቱ መሪዎች ትናንት ባደረጉት ስብሰባ “ከዚህ በኋላ ወደ ርካሽ የነዳጅ ዋጋ መመለስ አይታሰብም” ሲሉ ማሳሰባቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
- ጀርመን፤ የሩሲያ ጋዝ ወደ ሀገሯ በበቂ ሁኔታ ካልገባ ኢንዱስትሪዎች ሊዘጉ ይችላሉ ስትል አስጠነቀቀች
- የአውሮፓ ህብረት የሩሲያ የተፈጥሮ ጋዝን ለመተካት አፍሪካን እያማተረ ነው
የአውሮፓ ህብረት መሪዎች በብራሰልስ ባደረጉት ስብሰባ ዩክሬን ህብረቱን እንድትቀላቀል ድጋፋቸውን ከሰጡ ከአንድ ቀን በኋላ ትናንት አርብ ሩሲያ ልትፈጥረው በሚችለው የኢኮኖሚ ጫና ላይ ምክክር ማድረጋቸው ተሰምቷል።
የአውሮፓ ካውንስል ኃላፊ ቻርልስ ሚሽል በስብሰባው በሰጡት አስተያየት፤ የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ኢኮኖሚያቸውን በማቀራረብ የሚፈጠረውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
“የዋጋ ንረት የሁላችንም የራስ ምታት ነው” ያሉት ቻርልስ ሚሽል፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ወታደራዊ ዘመቻ የምግብ እና የኃይል ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል፤ ይህ ደግሞ ሁሉንም ዜጎች እና የንግድ እንቅስቀሴዎችን የጎዳ ነው ብለዋል።
ጉባኤው ጥቂት ተጨባጭ ውሳኔዎች እና እርምጃዎች ላይ መስማማቱ የተገለፀ ሲሆን፤ አውሮፓ ህብረት ኮሚሽን አቅርቦቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ የሚደረጉበትን መንግድ እንዲያፈላልግ ኃላፊነት ሰጥተዋል።
የአውሮፓ ሀገራት 40 በመቶ የተፈጠሮ ጋዝ ፍላጎታቸውን ከአውሮፓ የሚያገኙ ሲሆን፤ ጀርመን ደግሞ ለብቻዋ 55 በመቶውን ከሩሪያ ታሟላለች።
በጋዝ እጥረት ምክንያት ኢንዱስትሪዎች ሊዘጉ እንደሚችሉ የጀርመን ኢንዱስትሪ ሚኒስትር በትናንትናው እለት ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በሩሲያ ላይ ከ6 ሺህ በላይ ማዕቀቦች የተጣሉ ሲሆን ከ300 በላይ ዲፕሎማቶቿ ደግሞ ከተለያዩ ሀገራት ተባረው ወደ ሞስኮ ተመልሰዋል።
ሩሲያም የአጻፋ እርምጃ በመውሰድ ነዳጅ ገዢ ሀገራት በሩብል እንዲገዙ ውሳኔንም ያሳለፈች ሲሆን ጀርመን እና ጣልያን ማዕቀቡን ሳይጥሱ ከሩሲያ ነዳጅን በሩብል ለመግዛት ወስነው ነበር።