ግብጽ የ1 ቢሊዮን ዩሮ እርዳታ ቃል ተገባላት
ግብጽ ባለፈው ወር ከአለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ጋር የ8 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት መፈራረሟ ይታወሳል።
ህብረቱ እንደገለጸው ይህ የአንድ ቢሊዮን ዩሮ የአጭር ጊዜ እርዳታ በአጠቃላይ ለሀገሪቱ ከሚሰጠው የአምስት ቢሊዮን ዩሮ ብድር ፖኬጅ አካል ነው
ግብጽ የ1 ቢሊዮን ዩሮ እርዳታ ቃል ተገባላት።
የአውርፓ ህብረት በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው ግብጽ ኢኮኖሚያዋን ለማረጋጋት ለምታደርገው ጥረት የሚውል የአንድ ቢሊዮን ዩሮ (1.07 ቢሊየን ዶላር)ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
ግብጽ ባለፈው ወር ከአለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ጋር የ8 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት መፈራረሟ ይታወሳል።
ከአውሮፓ ህብረት የምታገኘው ይህ ድጋፍ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ኢኮኖሚዋ የተናጋባት ግብጽ ትብብሯ ከፍ እንዲል እና ስደትን እንድትቀንስ ይረዳታል ተብሏል።
ህብረቱ እንደገለጸው ይህ የአንድ ቢሊዮን ዩሮ የአጭር ጊዜ እርዳታ በአጠቃላይ ለሀገሪቱ ከሚሰጠው የአምስት ቢሊዮን ዩሮ ብድር ፖኬጅ አካል ነው።
ግብጽ ሌላ አራት ቢሊዮን ዩሮ ከ2024-2027 ባለው ጊዜ ውስጥ የረጅም ጊዜ እርዳታ ድጋፍ እንድታገኝ እቅድ መውጣቱን ህብረቱ ገልጿል።
እርዳታው በጋዛ ጦርነት፣ ሀውቲዎች በቀይ ባህር ላይ በሚሰነዝሩት ጥቃት እና በዩክሬን ጦርነት ምክንያት መንገራገጭ የታየበትን የግብጽ ኢኮኖሚ ለመታደግ ይለውላል ተብሏል።
የግብጽ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ የግብጽ ፓውንድ ዋጋ እንዲቀንስ መወሰኑን ተከትሎ ግብጽ ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት እርዳታ እና ብድር እያገኘች ነው።