የኬንያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ 2021 ኮሮና ቫይረስ ባስከተለው ጉዳት ምክንያት 135 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ማስመዝገቡ ይታወሳል
የአውሮፓ ህብረት የኬንያ አየር መንገድ የጥራት ደረጃ አላሟላም በሚል ፈቃዱን ሰርዟል፡፡
የአውሮፓ ህብረት አቪዬሽን ባለስልጣን በአውሮፓ ሀገራት ሰማይ ላይ የሚበሩ አውሮፕላን የጥራት ደረጃዎችን የሚገመግም እና የሚቆጣጠር ተቋም ነው፡፡
የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ኬንያ አየር መንገድ የአውሮፓ ህብረት አቪዮሽን የጥራት ደረጃን አላሟላም በሚል ምክንያት የበረራ ፈቃዱን ሰርዟል፡፡
አየር መንገዱ በበኩሉ የአውሮፓ ህብረት አቪዬሽን ባለስልጣን የመጋዘን መጠን እና የአየር ሙቀት መቆጣጠሪያ መሳሪያን እንዲለይ በመጠየቁ እና ይሄንን ባለማድረጉ ፈቃዱ ለመሰረዙ በምክንያትነት ጠቅሷል፡፡
የኬንያ አየር መንገድ የቴክኒክ ዳይሬክተር ለቢዝነስ ዴይሊ ለተሰኘው ሚዲና እንደተናገሩት የአውሮፓ ህብረት አቪዬሽን ባለስልጣን የጠየቀው የጥራት ደረጃን እንድናሟላ አሰራራችን አይፈቅድም ብለዋል፡፡
እስካሁን የአውሮፓ ህብረት አቪዬሽን ባለስልጣን የብቃት ደረጃን ያሟላ አንድም አውሮፕላን እንደሌለው የገለጸው አየር መንገዱ የአውሮፓን የጥራት ደረጃ ለማሟላት እየሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን የፈቃዱ መሰረዝ በአየር መንገዱ ገቢ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
የኬንያ አየር መንገድ በ2021 ዓመት ኮሮና ቫይረስ ባስከተለው ጉዳት ምክንያት 135 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ማስመዝገቡ አይዘነጋም፡፡