ሳይንቲስቶች 2023 በ125 አመታት ውስጥ ሞቃታማው አመት እንደሆነ ተናገሩ
ኮፐርኒከስ ኦብዞርቫቶሪ መረጃ መመዝገብ የጀመረው 1940 ነው
የኦብዞርቫቶሪው ምክትል ዳይሬክተር ሳማንታ ቡርገስ የጥቅምቱን የሙቀት መጠን "እጅግ በጣም ከባድ" ሲሉ ገልጸውታል
የአውሮፖ ሳይንቲስቶች 2023 በ125 አመታት ውስጥ ሞቃታማው አመት እንደሆነ ተናገሩ።
የአውሮፖ ህብረት ሳይንቲስቶች ይህ አመት በ125 አመታት ውስጥ ሞቃታማው አመት ሆኖ እንደሚመዘገብ እርግጠኞች እንደሆኑ ገልጸዋል።
ሳይንቲስቶቹ ይህን ያሉት ባለፈው ጥቅምት ወር የተመዘገበው ሙቀት በዓለም በእነዚህ አመታት ውስጥ ከተመዘገበው ከፍ ማለቱን የሚያሳይ መረጃ መውጣቱን ተከትሎ ነው።
የህብረቱ ኮፐርኒከስ ስፔስ ኦብዞርቫቶሪ ባለፈው ወር የተመዘገበው የሙቀት መጠን ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ የተመዘገውን ሙቀት በከፍጠኛ መጠን በልጦታል።
የኦብዞርቫቶሪው ምክትል ዳይሬክተር ሳማንታ ቡርገስ የጥቅምቱን የሙቀት መጠን "እጅግ በጣም ከባድ" ሲሉ ገልጸውታል።
ዳሬክተሯ ሪከርዱ በ0.4 ሴልሺየስ መሰበሩን እና ይህም ትልቅ ልዩነት መሆኑን ተናግረዋል
የሙቀት መጠኑ መጨመሩ በአልኒኖ ክስተት እና በሰው ልጅ መስተጋብር በሚፈጠረው የበካይ ጋዝ ልቀቶች ምክንያት ነው። በዓለምአቀፍ ደረጃ በጥቅምት የተመዘገበው የሙቀት መጠን ከ1850-1900 ድረስ በተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገው ይበልጣል።
ኦብዞሮቫተሪው ባወጣው መግለጫ 2023 በከፍተኛ ሙቀት ሪከርድ የሰበረ አመት ነው ብሏል።ቀደም ሲል የተመወገበው የሙቀት ሪከርድ አልኒኖ የተከሰተበት 2016 ነበር።
ኮፐርኒከስ ኦብዞርቫቶሪ መረጃ መመዝገብ የጀመረው 1940 ነው።
የአየር ሙቀት አማካኝ ከባለፈው ጥቅምቱ ወር በከፍተኛ መጠን የበለጠበት ወቅት ባለፈው መስሰረም ወር ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ አንደ ጎርፍ፣ ከፍተኛ ሙቀት እና በካናዳ የተከሰተውን አይነት ሰደድ እሳት እንዲከሰቱ መንስኤ ይሆናል። ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ ቃል ቢገቡም፣ እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም።