ዘለንስኪ ዩክሬንያውያን ሩሲያ በክረምት ለምትከተፍተው ጥቃት እንዲዘጋጁ አሳሰቡ
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተጀመረው ጦርነት ሞቅ፣ ቀዝቀዝ እያለ ቀጥሏል
ዘለንስኪ "ህዳርን እያጋመስነው ስለሆነ ጠላት በመሰረልማቶቻችን ላይ የድሮን እና የሚሳይል ጥቃት ሊያጠናክር ይችላል"ብለዋል
ዘለንስኪ ዩክሬንያውያን ሩሲያ በክረምት ለምትከተፍተው ጥቃት እንዲዘጋጁ አሳሰቡ።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ዩክሬናውያን ሩሲያ በመጭው ክረምት በመሰረተልማት ላይ ለምታደርሰው መጠነ ሰፊ ጥቃት ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስበዋል።
የጦሩ ቃል አቀባይ ከፍተኛ ጉዳት ባስተናገደችው የምስራቋ አቪዲቪካ ከተማ የነበረው ጥቃት ቀለል ብሎ የነበረ ቢሆንም በሚቀጥሉት ቀናት ሊባባስ እንደሚችል ተናግረዋል።
የዩክሬን ወታደራዊ ደህንነት በሩሲያ በተያችው የዩክሬኗ ሜሊቶፖል ከተማ ተቃዋሚ በሆኑ ኃይሎች ሶስት ሰዎች ተገድለዋል ብሏል።
ዘለሰንኪ ማስጠንቀቂያውን የተናገሩት ሩሲያ ከሰባት ሳምንት በኋላ በኪቭ ላይ የሚሳይል ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ ነው።
ዘለንስኪ "ህዳርን እያጋመስነው ስለሆነ ጠላት በመሰረልማቶቻችን ላይ የድሮን እና የሚሳይል ጥቃት ሊያጠናክር ይችላል"ብለዋል።
ሩሲያ ዩክሬንን ለማጥቃት እየተዘጋጀች መሆኗን የገለጹት ዘለንስኪ ዩክሬንም ጥቃቱን ለመመከት የወታደሮቿን አቅም በማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጋ እንደምትሰራ ገልጸዋል።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት 10ኛ ወሩን ይዞ በነበረበት ባለፈው ክረምት፣ ሩሲያ ከኢነርጂ ኔትወርክ ጋር በተያያዙ የኃይል ጣቢያዎች እና ሌሎች ተቋማት ላይ መጠነሰፊ ጥቃት ማድረሷ የሚታወስ ነው።
የዩክሬን የኢነርጂ ሚኒስቴር ጀርማን ጋሉሸንኮ ዩክሬን ለክረምቱ በቂ የሆነ የኢነርጂ ሀብት ቢኖራትም ሩሲያ የምትፈጽመው ጥቃት ምን ያህል ተጽእኖ ያሳድርበታል የሚል ጥያቄ እንዳላቸው ተናግረዋል።
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተጀመረው ጦርነት ሞቅ፣ ቀዝቀዝ እያለ ቀጥሏል።