ሞሀመድ ሳላህ ከክሎፕ ከፍተኛ አድናቆት የተቸረው በምን ምክንያት ነው?
የሊቨርፑሉ ተጨዋች ሞሀመድ ሳላህ ከአሰልጣኙ ጁርገን ክሎፕ ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል
ሊቨርፑል ብሬንትፎርድን 3-0 ማሸነፉን ተከትሎ ሳላህ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያስቆጠራቸው ግቦች 200 በመድረሳቸው ነው
የሊቨርፑሉ ተጨዋች ሞሀመድ ሳላህ ከአሰልጣኙ ጁርገን ክሎፕ ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል።
ክሎፕ አድናቆታቸውን የገለጹት እሁድ የተካሄደውን ጨዋታ ሊቨርፑል ብሬንትፎርድን 3-0 ማሸነፉን ተከትሎ ሳላህ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያስቆጠራቸው ግቦች 200 በመድረሳቸው ነው።
ሊቨርፑል ጨዋታውን በማሸነፉ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥም አስችሎታል።
በጨዋታው የ31 አመቱ ግብጻዊ በሁለቱ የጨዋታ አጋማሾች ሁለት ግቦችን አስቆጥራል።
ይህን ተከትሎ ሳላህ ለሊቨርፑል 198 እና ለቸልሲ 2 ግቦችን በማግባት በአጠቃላይ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያስቆጠራቸውን ግቦች 200 አድርሷል።
ክሎፕ ባለፈው የዝውውር መስኮት 150 ሚሊዮን ፖውንድስ ተቆብሎበት ነበር የተባለውን ሳላህን አድንቆታል።
"በእንግሊዝ የጎል ቁጥር 200 ደረስ፤ አውነት ነው? የተለየ ነው፤ ዛሬ ምርጥ ጨዋታ ተደርጓል። ሁለት ተጨዋቾች ሁል ጊዜ በዙሪያው አሉ፣ ኳሷን ይዞ ይጨዋታል።" በማለት ክሎፕ ለሳላህ አድናቆቱን ገልጿል።
በዚህ የጨዋታ እንቅስቃሴ የተደሰተው አሰልጣኝ ክሎፕ ከሊጉ መሪ ማንቸስተር ሲቲ ጋር የሚደረገው ጨዋታ መርሃግብር ላይ ቅሬታውን አሰምቷል።
ይህም ሆኖ ክሎፕ ቡድኑ በአውሮፖ ሊግ በቶሎዜ 3-2 ከተሸነፈ በኋላ ማንሰራራት መቻሉ እንዳስደሰተው ተናግሯል።