ለቻይና በመሰለል የተጠረጠረው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ
በቅርቡ ወራት ውስጥ ቻይና በምዕራብ አውሮፓ ሰላይ አሰማርታለች የሚለው ስጋት እየጨመረ መጥቷል
በአውሮፓ ህብረት ለጀርመኑ ቀኝ ዘመም ፓርቲ ተወካይ ለሆኑት አባል ረዳት ሆኖ ሲሰራ የነበረው ግለሰብ ለቻይና በመሰለል ተጠርጥሮ ጀርመን ውስጥ በቁጥጥር ውሏል
ለቻይና በመሰለል የተጠረጠረው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ።
በአውሮፓ ህብረት ለጀርመኑ ቀኝ ዘመም አሊያንስ ፎር ጀርመን ፓርቲ ተወካይ ለሆኑት አባል ረዳት ሆኖ ሲሰራ የነበረው ግለሰብ ለቻይና በመሰለል ተጠርጥሮ ጀርመን ውስጥ በቁጥጥር ውሏል።
አቃቤ ህግ ባወጣው መግለጫ የተያዘው ግለሰብ ጂያን ጂ. እንደሚባል እና በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ውስጥ ስለተደረጉ ውይይቶች ለቻይና ደህንነት መረጃ አሳልፎ በመስጠት ከሶታል።
ይህ ተጠርጣሪ በረዳትነት ሲያገለግሏቸው የነበሩት የህብረቱ ፓርላማ አባል የሆኑት ማክሲሚላን ራህ የጉኦን መያዝ በሚዲያ መስማታቸውን ገልጸዋል።
ራህ እንዳሉት በጉኦ ላይ የቀረበው ክስ የሚረጋገጥ ከሆነ አብሮ መስራታቸውን ያቆማሉ።
በቅርብ ወራት ውስጥ ቻይና በምዕራብ አውሮፓ ሰላይ አሰማርታለች የሚለው ስጋት እየጨመረ መጥቷል።
ሶስት ጀርመርውያን ለወታራዊ ስለላ ጥቅም ላይ ይውላል የተባለ መተግበሪያ አሳልፈው በመስጠት ተጠርጥረው በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተመሳሳይ ቀን የእንግሊዝ ፖሊስ በእንግሊዝ ፓርላማ አጥኝ ሆኖ ሲሰራ የነበረን ግለሰብ ጨምሮ ሁለት ሰዎችን ለቻይናው ገዥ ፓርቲ በመሰለል ጠርጥሮ ከሷል።
ሚስጥራዊ መረጃ ለቻይና አሳልፈው በመስጠት የተከሰሱት የ32 እና የ29 አመት እድሜ ያላቸው ግለሰቦች በቀጣይ አርብ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሏል።
በለንደን የሚገኘው የቻይና ኢምባሲ ቻይና የእንግሊዝን የደህንነት መረጃ እየሰረቀች ነው የሚለው ክስ "ፍጽም ፈጠራ" ነው ሲል አጣጥሎታል።