ደቡብ ኮሪያ ምዕራባውያን የሚጥሉትን ማዕቀብ በመደገፏ በሩሲያ "ወዳጅ ያልሆነች" ሀገር ተብላ ተፈርጃለች
በስለላ የተጠረጠረ ደቡብ ኮሪያዊ በሩሲያ በቁጥጥር ስር ዋለ።
በስለላ የተጠረጠረ ደቡብ ኮሪያዊ በሩሲያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ሮይተርስ የሩሲያ የመንግስት ዜና አግልግሎት የሆነውን ታስን ጠቅሶ ዘግቧል።
ይህ ግለሰብ ፓርክ ዋን ሱን እንደሚባል የገለጹት የጸጥታ አካላት በሩቅ ምስራቋ ቭላድቪቮስቶክ ከተማ ከያዙት በኋላ ለምርመራ ወደ ሞስኮ ልከውታል።
ሩሲያ ደቡብ ኮሪያዊን በስላላ ወንጀል ጠርጥራ ስትይዝ ይህ የመጀመሪያዋ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
ሮይተርስ በደቡብ ኮሪያ ኢምባሲ ስለጉዳዩ መረጃ ቢሞክርም ወዲያውኑ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጿል።
ደቡብ ኮሪያ፣ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በምታደርገው ጦርነት ምክንያት ምዕራባውያን የሚጥሉትን ማዕቀብ በመደገፏ በሩሲያ "ወዳጅ ያልሆነች" ሀገር ተብላ ተፈርጃለች። በተመሳሳይ ሩሲያም አሜሪካ ለሞስኮ የጦር መሳሪያ በማቅረብ ከምትከሳት ሰሜን ኮሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት አያጠናከረች ትገኛለች።
ወታደራዊ ግንኙነታቸውን እንደሚያጠናግሩ የሚገልጹት ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ግን የጦር መሳሪያ ማቅረቡን ጉዳዩ አስተባብዋል።