ሀገሪቱ የአውሮፓን እሴቶች ለመጠበቅ ከሩሲያ ጥቃቶች ማሸነፍ አለባት ተብሏል
የአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ከሁለቱ ወገኖች የመሪዎች ጉባኤ በፊት ዩክሬን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድጋፍ አላት ብለዋል።
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኤርሰላ ፎን ደር ሌየን በሚቀጥለው ሳምንት ከሚካሄደው የአውሮፓ ህብረት እና የዩክሬን የመሪዎች ጉባኤ አስቀድሞ እንደተናገሩት ዩክሬን ከህብረቱ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ድጋፍ እንዳላት አስታውቀዋል።
ሀገሪቱ የአውሮፓን እሴቶች ለመጠበቅ ከሩሲያ ጥቃቶች ማሸነፍ አለባት ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቷ በጀርመን በተደረገ ዝግጅት ላይ ባደረጉት ንግግር "ያለምንም ማቅማማት ከዩክሬን ጎን እንቆማለን" ብለዋል።
ዩክሬን "ለጋራ እሴቶቻችን እየታገለች ነው። ለዓለም አቀፍ ህግ መከበር እና ለዲሞክራሲ መርሆዎች እየታገለች ነው። ለዚህም ነው ዩክሬን ይህንን ጦርነት ማሸነፍ ያለባት" ሲሉ ተናግረዋል።
ቮን ደር ሌየን እና ሌሎች የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽነሮች በፈረንጆች የካቲት ሦስት የአውሮፓ ህብረት እና የዩክሬይን ስብሰባ እንደሚያካሂዱ ይጠበቃል።