የአውሮፓ ህብረት ለሩሲያ ድሮኖች አቅረባለች ባላት ኢራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ሊጥል እንደሚችል አስጠነቀቀ
የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ አውሮፓ ተጨማሪ የአየር መከላከያ እና የጦር መሳሪያ እንዲያቀርብላቸው ጠይቀዋል
ቴህራን መሳሪያ የታጠቁ ድሮኖችን ለሞስኮ አቀረበች የሚለውን የዩክሬን ክስ ውድቅ አድረገዋልች
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለሩሲያ የጦር መሳሪያ አቅረባለች በሚል ኢራን ላይተጨማሪ ማዕቀብ ሊጥል እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
የዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭና ሌሎች ዩክሬን ከተሞች ላይ ሰኞ አለት በተሰነዘርው ጥቃትና በደረሰው ፍንዳታ የኢራን ሻሄድ 136 ድሮች ጥቅም ላይ ውለው ሊሆን እንደሚችል የዐይን እማኞች መናገራቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
በዚህም ሩሲያ የኢራን ድሮኖችን እየተጠቀመች ነው የምትለው ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት በቴህራን ላይ ተጨማሪ ማዕከቀብ እንዲጥል በመወትወት ላይ ናት።
የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲምትሪ ኩሌባ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት "የአውሮፓ ህብረት ለሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በማቅረብ በኢራን ላይ ማዕቀብ ሊጥል ይገባል” ብለዋል።
ህብረቱ ተጨማሪ የአየር መከላከያ እና የጦር መሳሪያ ለዩክሬን እንዲያርብም ጭምር ጠይቀዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ።
ቢዘህም መሰረት በርካታ የህብረቱ ሚኒስትሮች ኢራን በጦርነቱ ውስጥ ያላትን “ግልጽ” ተሳትፎ በመጥቀስ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል።
የአውሮፓ ህብረት መሪዎች በዚህ ሳምንት መጨረሻ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ተጨማሪ እርምጃዎችን ለመውሰድ ከስምመነት ሊደርሱ እንደሚችሉ ሮይተርስ ከህብረቱ የውስጥ ሰዎች ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክት ዘግቧል።
ዬክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ባሳለፍነው ሳምንት በሰጡት መግለጫ ፤ሩሲያ የኢራንን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ጥቃት እያደረሰችብን ነው ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡
ጥቃቱ በተለያዩ የዩክሬን ከተሞች ላይ ያነጣጠረ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የዩክሬን የኢነርጂ መሰረተ ልማቶችን ኢላማ ያደረገ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡
የአሁን ተከታታይ የሰው አልባ አውሮፕላን ሚሳዔሎች ድብደባ የጦርነቱ መጀመሪያ አከባቢ ሞስኮ ኪቭን ለመቆጣጠር ታደርገው የነበረ መጠነ ሰፊ ጥቃት አይነት ነው ተብሏል።