በአውሮፓ በተከሰተው ድርቅ የኃይል እጥረት ያጋጥማል ተብሎ ተሰግቷል
በአውሮፓ አህጉር አሁን ላይ የተከሰተው ድርቅ በ 500 ዓመት ውስጥ ያጋጠመ “አስከፊ አደጋ” መሆኑን የአውሮፓ ህብረት ገለጸ፡፡
አህጉሩ ያጋጠመው አስከፊ ድርቅ በመሆኑ በርካታ ሀገራት የቅድመ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ማውጣታቸው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የአውሮፓ ክፍል አሁን ላይ ድርቁን ተከትሎ አስቸኳይ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መልዕክት መተላለፉ እየተገለጸ ነው፡፡
የአውሮፓ የድርቅ ተከታታይ መምሪያ እንዳስታወቀው አሁን ላይ ከአህጉሩ 47 በመቶ የሚሆነው በማስጠንቀቂያ መልዕክት ላይ ነው፡፡ በአውሮፓ አህጉር በአፈር ላይ ምንም እርጥበት እንደሌለም የገለጸው መምሪያው በክፍለ ዓለሙ ካሉት ሀገራት መካከል 17 በመቶ የሚሆኑት የድርቅ ማስጠንቀቂያ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
በአውሮፓ አህጉር በ 2022 በርካታ ቦታዎች በድርቅ መጠቃታቸው የተገጸ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ ድርቁ እየተስፋፋ ነው ተብሏልለ፡፡ በ500 ዓመታት ውስጥ የተከሰተ አስከፊ ድርቅ ነው የተባለው የአሁኑ ክስተት ነሐሴ ወር ላይ መባባሱን የአውሮፓ ህብረት አስታውቋል፡፡
በምዕራብ አውሮፓ የሚገኙት ሀገራት ከወትሮው በተለየ ደረቅ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ በአውሮፓ የተከሰተው ይህ ድርቅ የጀልባዎችን ጉዞ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ምርትን እያስተጓጎለ መሆኑን ህብረቱ አስታውቋል፡፡ ከዚህ ባለፈም ተከስቷል የተባለው አስከፊ ድርቅ በሰብል ምርቶች ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል ተብሏል፡፡
የአውሮፓ ኮሚሽን ድርቁ በ 500 ዓመት ውስጥ እጅግ አስከፊው ነው ሲል የገለጸው ሲሆን ይህንን የተመለከተ መረጃ የፈረንጆቹ 2022 ከመጠናቀቁ በፊት ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡
በአህጉሩ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በ 2022 የእህል ምርት ላይ ከፍተኛ ቅናሽ እንደሚኖር ያጠበቃል ተብሏል፡፡ የበቆሎ ምርት በ 16 በመቶ፤ የባቄላ ምርት በ 15 በመቶ፤ የሱፍ ምርቶች ደግሞ የ 12 በመቶ ቅናሽ እንደሚኖራቸው ተገምቷል፡፡