የአውሮፓ ሀገራት ለታዳሽ ሀይል ከሁለት ትሪሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚያደርጉ ተገለጸ
ሀገራቱ ባለፈው ዓመት ለነዳጅ ግዢ ከ800 ቢቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርገዋል ተብሏል
የአውሮፓ ህብረት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የካርበን ግብር ማስከፈል ጀምሯል
የአውሮፓ ሀገራት ለታዳሽ ሀይል ከሁለት ትሪሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚያደርጉ ተገለጸ፡፡
የዓለማችን ሀብታሙ አህጉር አውሮፓ እንደ ማንኛውም የዓለማችን ክፍል በአየር ንብረት ለውጥ እየተፈተነ ይገኛል፡፡
አህጉሩ በተለይም በሙቀት መጨመር፣ በቅዝቃዜ ፣ በድርቅ እና በውሃ መጥለቅለቅ በርካታ ጉዳቶችን በማስተናገድ ላይ ሲሆን ባሳለፍነው ክረምት ከፍተኛ የተባለውን ሙቀት አስተናግዷል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስም በታዳሽ የሀይል ምንጭ ላይ ብዙ ለውጦችን በማድረግ ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ለአብነትም እስከ ፈረንጆቹ 2040 ድረስ ሁለት ነጥብ 1 ትሪሊዮን ዶላር ለታዳሽ ሀይል ለማውጣት ማቀዱን አስታውቋል፡፡
ለዓለማችን የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ለመስጠት 2 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ
ሀገራቱ የሀይል አማራጫቸውን ከነዳጅ እና ድንጋይ ከሰል ወደ ጸሀይ፣ ንፋስ እና ከውሀ በሚገኝ ሀይል የማድረግ እቅድ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡
እንደ ፎርብስ ዘገባ ከሆነ የአውሮፓ ሀገራት የሀይል ምንጫቸውን ወደ ታዳሽ ሀይል ለመቀየር በየዓመቱ ከ100 እስከ 147 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ይህም አውሮፓ የሀይል ምንጯን ሙሉ ለሙሉ ከታዳሽ ሀይል እንድታገኝ የሚያስችላት ሲሆን ረጅም ዓመት ያገለገሉ እና በጋዝ የሚሰሩ ኢንዱስትሪዎች ቀስ በቀስ ወደ ታዳሽ ሀይል መቀየር ያስችላል ተብሏል፡፡
አውሮፓ ባሳለፍነው ዓመት ብቻ 833 ቢሊዮን ዶላር ለጋዝ ሸመታ ወጪ አድርገዋል የተባለ ሲሆን የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ደግሞ ለወጪው መጨመር ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የአውሮፓ ህብረት በካይ ጋዝን ለመከላከል ወደ አህጉሪቱ በሚገቡ እንደ ሲሚንቶ፣ ጋዝ እና ሌሎች ከፍተኛ የካርበን ጋዝ ባላቸው ምርቶች ላይ አዲስ ቀረጥ ማስከፈል ጀምሯል፡፡