አውሮፓ ከፊቱ ፈጣን ድርቅ ተደቅኖበታል ተባለ
በክፍለ ዘመኑ መጨረሻ በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ የእርሻ መሬቶች እስከ 53 በመቶ የሚደርስ ፈጣን የመድረቅ እድል አላቸው ተባለ
ድርቁ የምግብና የኃይል አቅርቦቶች ላይ ጫና በማሳደር ዋጋም እንዲጨምር ያደርጋል ተብሏል
በአውሮፓ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሊከሰት የሚችል ፈጣን የድርቅ አደጋ እንደተደቀነ ተነግሯል።
በአለም ኢኮኖሚክ ፎረም ይፋ የተደረገ አዲስ ጥናት በክፍለ ዘመኑ መጨረሻ በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ የእርሻ መሬቶች በዓመት እስከ 53 በመቶ የሚደርስ ፈጣን የመድረቅ እድል አላቸው ብሏል።
ከዓመታት በፊት የመሬቶች የመድረቅ እድል 32 በመቶ እንደነበር ተነግሯል።
የድርቁ ውጤት የምግብ ምርትን፣ ኃይል እና የውሃ አቅርቦቶችን እየጨመረ በሚሄድ ጫና ውስጥ ይጥላቸዋል። የምርቶቹ ዋጋም ይጨምራል ተብሏል።
በ2017 በዳኮታ እና ሞንታና የተከሰተው ፈጣን ድርቅ በአሜሪካ ብቻ 2.6 ቢሊዮን ዶላር በግብርና ላይ ጉዳት አድርሷል።
ከተሽከርካሪዎች፣ ከኃይል ማመንጫዎች እና ሌሎች ልቀቶች የሙቀት አማቂ ጋዝ በከፍተኛ ፍጥነት የሚቀጥል ከሆነ በአብዛኛዎቹ ሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ ያሉ የእርሻ መሬቶች 49 በመቶ እና 53 በመቶ በፍጥነት የመድረቅ እድል እንደሚኖራቸው ጥናቱ ገልጿል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚጠበቀው ድርቁ በዋናነት በአውሮፓ እና አማዞን እንደሚከሰት ተነግሯል።
የልቀት መጠን መቀነስ የተንጃበበውን አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስ ይችላል ቢባልም፤ ነገር ግን ጥናቱ በዝቅተኛ የልቀት ሁኔታ ውስጥም በዓለም አቀፍ ደረጃ የድንገተኛ ድርቅ ክስተቶች በስድስት በመቶ ገደማ ይጨምራሉ።
ፈጣን ድርቅ ሰዎች እንዲሰቃዩ እና ሰብሎች እንዲጠፉ አድርጓል። በ2022 ፈጣን ድርቅ ከ90 በመቶ በላይ የአሜሪካን የግብርና ምርት በሚያጓጉዘው ሚሲሲፒ ወንዝ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።