ድርቅ በተከሰተበት በቦረና ዞን ያቤሎ ዝናብ መዝነቡ ተገለጸ
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ በተለይም በእንስሳት ላይ ከባድ ጉዳት አስከትሏል
በድርቁ የተከሰተው ጉዳት ከተሰማ በኋላ መንግስት እና ግለሰቦች በገንዘብ እና በቁስ ሰብአዊ እርዳታ በማድረስ ላይ ናቸው
ድርቅ ጉዳት ባደረሰበት ቦረና ዞን ዝናብ መዝነቡ ተገለጸ።
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ በተለይም በእንስሳት ላይ ከባድ ጉዳት አስከትሏል።
በድርቁ የተከሰተው ጉዳት ከተሰማ በኋላ መንግስት እና ግለሰቦች በገንዘብ እና በቁስ ሰብአዊ እርዳታ በማድረስ ላይ ናቸው።
በዞኑ በያቤሎ እና አካባቢው የሚኖሩ ሰዎችን ተስፋ ያለመልማል የተባለ ዝናብ ከትናንት በስትያ መዝነቡን ኢዜአ ዘግቧል።
በ13 ወረዳዎች የተዋቀረው ዞኑ ባለፈው አመትም የድርቅ አደጋ አጋጥሞት ነበር።
የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ዝናብ ዘንቦ የነዋሪዎችን ተስፋ አለምልሞ ነበር።
የቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጃርሶ ቦሩ በወቅቱ በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ዝናብ መጣሉን ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸው ነበር፡፡
ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ መጠን ያለው ዝናብ በዞኑ መመዝገቡን ያነሱት አቶ ጃርሶ በዚህም ኩሬዎች ውኃ መያዛቸውን፣ ውኃ መገኘቱንና ለሕብረተሰቡ ተስፋ መስጠቱን ነበር የገለጹት፡፡
የበልግ ዝናብ ወቅተን የሚጠብቁት የቦረና ዞን አካባቢዎች በየአመቱ ዝናብ ባለመዝነቡ እንስሳቱን ለእልቂት በመዳረግ ሰዎችን ለማህበራዊ ቀውስ ሲዳርግ ቆይቷል።
" የዝናብ በመመለሱ ተደስተናል፤ ይህም ተስፋ እንድንሰንቅ አድርጎናል" ሲሉ ነዎሪዎች የኢዜአ ተናግረዋል።
በዞኑ 867ሺ የድርቅ አደጋው ተጎጂ ናቸው።
የኦሮሚያ ክልል መንግስት በድርቁ ጉዳት ለደረሰባቸው የዞኑ ነዋሪዎች ድጋፍ በማሰባሰብ እያደረሰ እንደሚገኝ ገልጿል።