የብክለት መናኸሪያ የሆኑ የአውሮፓ ከተሞች
የአውሮፓ ከተሞች በ2023 የአየር ብክለት መጠን ይፋ ተደርጓል
የጣሊያኗ ሚላን ከተማ 19.5 ማይክሮ ግራም በማስመዝገብ የአየር ብክለት በከፍተኛ ሁኔታ ያለባት የአውሮፓ ከተማ ሆናለች
በብሪታንያ መንግስት የተደረገ ጥናት በአብዛኞቹ የአውሮፓ ከተሞች በ2023 የአየር ብክለት መጠን ይፋ ተደርጓል።
ታይም አውት በተባለ መጽሄት የወጣው የጥናቱ ሪፖርት፤ በአውሮፓ በአየር ብክለት እየተቸገሩ ያሉ ሀገራትን ዘርዝሯል።
የዓለም የጤና ድርጅት ለሰው ልጅ ጤና አደገኛ በሚል ለአየር ብክለት አመላካቾችን ያወጣል።
በድርጅቱ አስጊ የተበከለ አየር ከአምስት ማይክሮ ግራም በላይ ሲሆን፤ ይህን ተመርኩዞ በተሰራው ጥናት ሚላን ከተማ አንደኛ ሆናለች።
የጣሊያኗ ሚላን ከተማ 19.5 ማይክሮ ግራም በማስመዝገብ የአየር ብክለት በከፍተኛ ሁኔታ ያለባት የአውሮፓ ከተማ ሆናለች።
የሚላን ብክለት በዓለም የጤና ድርጅት ከተቀመጠው የአየር ብክለት መጠን በአራት እጥፍ ይበልጣል። በሁለተኛ ደረጃ የአውሮፓ በህዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆነችው አቴንስ ተቀምጣለች።
የግሪኳ አቴንስ 13.6 ማይክሮ ግራም የተበአለ አየር የተገኘባት ሲሆን፤ በዓለም የጤና ድርጅት ጤናማ ተብሎ ከተቀመጠው መጠን በሁለት እጥፍ የሚበልጥ የአየር ብክለት አስመዝግባለች።
ፕራግ፣ ባርሴሎና እና በርሊን በሦስተኛ ደረጃ በአውሮፓ የአየር ብክለት ያለባቸው ከተሞች ሆነዋል።