የአውሮፓ ሀገራት በሰሜን ኮሪያ ኢምባሲዎቻቸውን በመክፈት ላይ እንደሆኑ ተገለጸ
ጀርመን፣ ብሪታንያ፣ ስዊድን እና ሌሎች ሀገራት ኢምባሲዎቻቸውን በፒዮንግያንግ በመክፈት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል
ሀገራቱ ከሶስት ዓመት በፊት ነበር ኢምባሲዎቻቸውን ለመዝጋት የተገደዱት
የአውሮፓ ሀገራት በሰሜን ኮሪያ ኢምባሲዎቻቸውን በመክፈት ላይ እንደሆኑ ተገለጸ፡፡
የአውሮፓ ሀገራት በሰሜን ኮሪያ መዲና ፒዮንግያንግ ኢምባሲዎቻቸውን ለመክፈት እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
እንደ ሮይተርስ ዘገባ በአውሮፓ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ የሖነችው ጀርመን በፒዮንግያንግ ኢምባሲዋን ለመክፈት የዲፕሎማት ልኡኳን ወደ ሰሜን ኮሪያ ልካለች፡፡
ወደ ፒዮንግያንግ ያመሩት የጀርመን ዲፕሎማቶች በሰሜን ኮሪያ ቆይታቸው ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ኢምባሲው መከፈት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተመካክረው እንደሚመለሱም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ሌላኛዋ አውሮፓዊት ሀገር ብሪታኒያ ኢምባሲዋን በሰሜን ኮሪያ መዲና ለመክፈት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንዳለች ተገልጿል፡፡
የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢምባሲያችንን በፒዮንግያንግ ለመክፈት ጥረቶችን እያደረግን ነው ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል፡፡
የሰሜን ኮሪያ መሪ ወንድ ልጃቸውን ለምን ከህዝብ እይታ ደበቁ?
ለዚህ ተልዕኮ ሲባልም ከለንደን ወደ ፒዮንግያንግ የሚያመራ ልኡክ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ሲልም ቃል አቀባዩ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡
የጠመድ ተቋማትን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በሰሜን ኮሪያ ኢምባሲያቸውን ከፍተው የነበረ ቢሆንም ከአራት ዓመት በፊት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ዘግተው ለመውጣት ተገደው ነበር፡፡
ሌላኛዋ ሀገር ስዊድንም በሰሜን ኮሪያ ኢምባሲዋን ለመክፈት ፍላጎት እና ጥረቶችን በማድረግ ላይ መሆኗን አስታውቃለች፡፡
በአሁኑ ወቅት በሰሜን ኮሪያ ኢምባሲ ያላቸው ሀገራት ሩሲያ፣ ቻይና፣ ኩባ እና ሞንጎሊያ ብቻ ናቸው፡፡