የሰሜን ኮሪያ መሪ ወንድ ልጃቸውን ለምን ከህዝብ እይታ ደበቁ?
የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሚስጥር ደብቀው ያስቀመጡት ወንድ ልጅ አላቸው ተብሏል
ኪም ወንድ ልጃቸው ወፍራም ባለመሆኑ ከእይታ መደበቃቸውን የደቡብ ኮሪያ የስለላ ባለስልጣን ተናግረዋል
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከህዝብ እይታ የደበቁት ወንድ ልጅ እንዳላቸው የቀድሞ የደቡብ ኮሪያ የስለላ ባለስልጣን ከሰሞኑ ተናግረዋል።
ኪም ጆንግ ኡን ወንድ ልጃቸው እንደ እሳቸው አሊያም እንደ እህቱ ወፍራም ባለመሆኑ እና ማራኪ እይታ የለው በሚል ከእይታ መደበቃቸውን ኮርያ ታይምስ ጋዜጣ በጡረታ የወጡ የብሄራዊ መረጃ አገልግሎት ባለስልጣን ቾይ ሱ-ዮንግን ጠቅሶ ዘግቧል።
የደቡብ ኮሪያ የቀድሞ የስለላ ኃላፊ አክለውም የኪም ወንድ ልጅ አያቱ የሆኑትን ኪም ኢል ሱንግን አለመምሰሉም ልጁ ከህዝብ እይታ እንዲደበቅ ምክንያት ሊሆን እንደሚችልም ተናግረዋል።
የኪም ሚስጥራዊ ወንድ ልጅ ፎቶ ግራፍም የለውም የተባለ ሲሆን፤ በመልክ ግን አባቱን በወጣትነቱ የነበረውን መልክ ሊመስል እንደሚችልም ነው የተገለጸው።
የሰሜን ኮሪያን ፖለቲካ የሚከታተለው ማይክል ማደን፤ ኪም ጆንግ ኡን ወደ ስልጣን ሲመጡ ቀጭን ነበሩያለ ሲሆን፤ ነገር ግን አባት እና አክስቱ ለስልጣን ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ ሰውነቱን ወፍራም መሆን እንዳለበት ነግረውት እንደነበረ ያስታውሳል።
በኮርያ ታይምስ ጋዜጣ ዘገባ መሰረት የሰሜን ኮሪያ ለመምራት የሀገሪቱ መስራች ከሆኑት ከኪም ኢል ሱንግ ጋር በመልክ እና በሰውነት ውፍረት መመሳሰል አስፈላጊ መስፈርት ተደርጎ ይወሰዳል።
የወቅቱ መሪ በእራሳቸው እና በአያታቸው ኪም ኢል ሱንግ መካከል ተመሳሳይነት አላቸው በሚል የሚነሳ ሲሆን፤ በቀጣይም ሰሜን ኮሪያ እንደ ኪም ጆንግ-ኡን ሴት ልጅ ያሉ ውፍረት ያላቸው መሪዎች ሊታዩ እንደሚችሉ ተነግሯል።
ጆ ሄ የተባለችው የኪም ጆንግ ኡን ሴት ልጅ በሰውነቷ ውፍረት ምክንያት በአባቷ ተመረጭ እንደሆነች የተገመተ ሲሆን፤ ከ2022 ወዲህም በስፋት ከበኣቷ ጋር ትታያለች።
የደቡብ ኮሪያ የስለላ አገልግሎት ኪም ጆንግ-ኡን ሶስት ልጆች አላቸው እና ሚስጥራዊ ወንድ ልጅ የበኩር ወንድ ልጅ፣ ከዚያም ሴት ልጅ ኪም ጆ-ኤ ሁለተኛው ልጅ እንዲሁም ሶስተኛው ጾታው ያልታወቀ ልጅ እንደሆነ ያምናሉ።