ጀርመን እና ስፔን ብዙ ስደተኞችን የተቀበሉ ሀገራት ሲባሉ ሀንጋሪ ደግሞ 29 ስደተኞችን ብቻ ተቀብላለች ተብሏል
ብዙ ስደተኞችን የተቀበሉ የአውሮፓ ሀገራት
የዓለማችን ዋነኛ የስደተኞች መዳረሻ በሆነው አውሮፓ የጥገኝነት ጠያቂ ዜጎች ቁጥር እንደቀነሰ ተገልጿል።
የአውሮፓ ህብረት ጥገኝነት ጠያቂዎች ኤጀንሲ ባወጣው ሪፖርት በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ውስጥ በአውሮፓ የጥገኝነት ጥያቄ ያቀረቡ ስደተኞች ቁጥር አንድ ሚሊዮን ነው።
ይህም በ2023 የስደተኞች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር በ12 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ተብሏል።
ጀርመን አሁንም ዋነኛ የስደተኞች ተቀባይ ሀገር ስትሆን በተጠቀሰው ዓመት 235 ሺህ ስደታኞችን ተቀብላለች።
የአውሮፓ ህብረት ስደተኞች እቅድን የተቃወመችው ሀንጋሪ በተጠቀሰው ዓመት ውስጥ 29 ስደተኞችን ብቻ መቀበሏን ዶቸቪሌ ዘግቧል፡፡