አሜሪካ ባለፉት 100 ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ ከ76 ሺህ በላይ ስደተኞችን ስታባርር ነበር
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ከሁለት ሳምንት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያካሄደች ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን አሸንፈዋል፡፡
የምርጫው ውጤት ከታወቀ በኋላ የብዙዎች ትኩረት የሆነው ጥር ላይ ስራ የሚጀምረው አዲሱ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር ምን ይመስላል ሚለው ሆኗል፡፡
በተለይም ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ለአሜሪካዊያን ቃል ከገቡባቸው ጉዳዮች መካከል የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው እና በአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ስደተኞችን አባርራለሁ ማለታቸው አንዱ ነው፡፡
ይህን ተከትሎም በአሜሪካ የሚኖሩ ነገር ግን የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኞች ተገደን ልንባረር እንችላለን የሚል ስጋት ውስጥ እንደሆኑ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እንደ ፒው ጥናት ማዕከል ከሆነ አሜሪካ ባለፉት 126 ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ ከ6 ሺህ በላይ ስደተኞችን ስታባርር በአጠቃላይ 8 ነጥብ 3 ሚሊዮን ስደተኞችን በግዳጅ ከሀገሯ አባራለች፡፡