አምንስቲ ኢንተርናሽናል በአፍሪካ የፕረስ ነጻነትን አስመልክቶ ጥናቱን ይፋ አድርጓል
ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ በርካታ ሀገራት የፕሬስ ነጻነት ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ተገለጸ።
የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ጥቃት እየተፈጸመበት መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።
ድርጅቱ ከደቡባዊ አፍሪካ ሚዲያ ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ባስጠናው ጥናት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ የፕረስ ነጻነት ችግር ውስጥ ነው ብሏል።
በፈረንጆቹ 2022 ብቻ 29 ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ መታሰራቸውን በጥናቱ ተጠቁሟል።
ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ዚምባብዌ፣ ታንዛኒያ ፣ ቡሩንዲ ፣ማላዊ እና ሌሎችም ሀገራት የፕረስ ነጻነት ችግሩ የከፋባቸው ናቸውም ተብሏል።