በባለፈው የሻምፒዮንሺፕ ዘመን ወደ ሁለተኛ ዲቪዥን ከመውረድ ለጥቂት ያመለጠው ኢቨርተን ነጥቡ ከመቀነሱ በፊት በሊጉ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ነበር
ኢቨርተን 10 የፕሪሜየር ሊግ ነጥብ ተቀነሰበት።
ኢቨርተን የፕሪሜየር ሊግ ትርፍ እና ዘላቂነት (ፒኤስአር) ህጎችን በመጣሱ 10 ነጥብ እንደተቀነሰበት ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
በተላለፈው ውሳኔ "መደንገጡን እና ቅር መሰኘቱን" የገለጸው ኢቨርተን ቅሬታ አቀርባለሁ ብሏል።
ክለቡ የተላለፈው ቅጣት ክብደት እና አደገኛነት ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ነው ሲል ተቃውሟል።
ገለልተኛ በሆነ ኮሚሽን የተደረገው የነጥብ ቅነሳ ወዲያውኑ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ትልቁ ቅጣት ነው ተብሏል።
ይህ ቅጣት የሲአን ዳይችን ቡድን ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ያደርገዋል።
እንደፕሪሚየር ሊጉ ከሆነ ለአምስት ቀናት በተደረገ የማጣራት ስራ ኤቨርተን የሊጉን ፒኤስአር ህጎች መጣሱን አምናል።
ኮሚሽኑ "በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የኢቨርተን የፒኤስአር ስሌት 124.5 ሚሊዮን ዩሮ ኪሳራ ማስከተሉን እና ይህም ከተፈቀደው 105 ሚሊዮን ዩሮ ድርሻ በላይ መሆኑን" አረጋግጧል።
በባለፈው የሻምፒዮንሺፕ ዘመን ወደ ሁለተኛ ዲቪዥን ከመውረድ ለጥቂት ያመለጠው ኢቨርተን ነጥቡ ከመቀነሱ በፊት በሊጉ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ነበር።