ስፖርት
የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ሃላፊ ሴኔጋላዊው ላሚን ዲያክ አረፉ
የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ሃላፊ በሙስና ተከሰው የ4 ዓመት የቤት ውስጥ እስረኛ ነበሩ
ላሚን ዲያክ በ88 ዓመታቸው ነው ሴኔጋል መዲና ዳካር በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ያረፉት
የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ሃላፊ ላሚን ዲያክ ሕይወታቸው አለፈ፡፡
ሴኔጋላዊው የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ሃላፊ ላሚን ዲያክ በ88 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ላሚን ዲያክ የዓለም አትሌቲክስን ከፈረንጆቹ 1999 እስከ 2015 ዓመት ድረስ በሃላፊነት ሲመሩ ቆይተው በሙስና ተጠርጥረው ከስልጣን ተነስተዋል፡፡
ላሚን ዲያክ ፈጽመውታል በተባለው የሙስና ወኝጀል የ4 ዓመት የቤት ውስጥ እስር ተፈርዶባቸው በሴኔጋል መዲና ዳካር ከተማ የእስር ጊዜያቸውን በመወጣት ላይ ነበሩ፡፡
የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ሃላፊ በተፈጥሮ መንገድ ህይወታቸው ማለፉን ልጃቸው ፓፓ ማሳታ ዲያክ ለብዙሃን መገናኛዎች ተናግረዋል፡፡
በሴኔጋል ተወልደው የደጉት ላሚን ዲያክ የአገሪቱ መዲና የሆነችው ዳካርን በከንቲባነት ከፈረንጆቹ 1978 እስከ 1980 ዓመት ድረስ ከንቲባ ሆነው አገልግለዋል፡፡