ለባለን ደ ኦር አሸናፊነት እነ ማን ሜሲን ተቀናቀኑ?
ሊዋንዶውስኪ የዓመቱ ምርጥ አጥቂ ሆኖ ሲመረጥ የሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ቼልሲ ደግሞ የአመቱ ምርጥ ቡድን ተብሏል
ሊዮኔል ሜሲ ባንደ ኦርን ለ7ኛ ጊዜ አሸንፎ አዲስ ክብረ ወሰንን አስመዝግቧል
ሊዮኔል ሜሲ፤ ሮበርት ሊዋንዶውስኪን በመብለጥ ባለን ደ ኦርን ለ7ኛ ጊዜ አሸነፈ፡፡
ሽልማቱን ደጋግሞ በማሸነፍ ሪከርዱን የያዘው ሜሲ ፒኤስጂን ከመቀላቀሉ በፊት ባለፈው የውድድር ዓመት ለባርሴሎና 38 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡
የውድድር ዓመቱ ሜሲ ልክ እንደቀደሙት ዓመታት ሁሉ ደምቆ የታየበት አይደለም፡፡ ሆኖም ለአንዳንዶች የህይወት ዘመን ስኬት ሊሆኑ የሚችሉ ድሎችን አስመዝግቧል፡፡
ሊዮኔል ሜሲ በሁለት ዓመት ኮንትራትን ፒኤስጂን ተቀላቀለ
ባርሳ አትሌቲኮ ቢልባኦን አሸንፎ የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫን እንዲያነሳ አስደናቂ ብቃትን ከማሳየትም በላይ ጎል አስቆጥሯል፡፡
ለብዙ ዓመታት ሳያሳካው ቀረውን የኮፓ አሜሪካን ዋናጫንም አሳክቷል፡፡ ይህ ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ጋር ያሳካው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ድሉ ነው፡፡
ለአርጀንቲና በተሰለፈባቸው የውድድሩ ጨዋታዎች አምስት ጎሎችን ከማስቆጠርም በላይ አራት ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች ኢታሎ ቫሳሎ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ከቀድሞ የክለብ ባልደረባው ከሉዊስ ሱዋሬዝ እጅ የወርቅ ኳስ ሽልማቱን ተቀብሏል፡፡
ምርጡ ፖላንዳዊ የባየር ሙኒክ አጥቂ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ፣ ግብጻዊው የሊቨርፑል አጥቂ መሃመድ ሳላህ እና ሌላኛው የቼልሲ ተጫዋች ጣልያናዊው ጆርጊንሆ የሜሲ ተቀናቃኝ ሆነው ቀርበው ነበር፡፡
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ብዙ እግር ኳስ ቡድኖች የሌሏቸው ዋንጫዎች አሉት
በተለይ ከአሁን ቀደምም ለሽልማቱ ታጭቶ የነበረው ሊዋንዶውስኪ እና ከጣልያን ብሔራዊ ቡድን ጋር የአውሮፓ ዋጫን ከቼልሲ ጋር ደግሞ ሻምፒዮንስ ሊግን አንስቶ የነበረው ጆርጊንሆ ለአሸናፊነት ተጠብቀው ነበር፡፡
ሆኖም ሊዮኔል አንደሬስ ሜሲ ሽልማቱን ለ7ኛ ጊዜ አሸንፏል፡፡
ሊዋንዶውስኪ የዓመቱ ምርጥ አጥቂ ሆኖ ሲመረጥ የሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ቼልሲ ደግሞ የአመቱ ምርጥ ቡድን ተብሏል፡፡
የሽልማቱ አሸናፊዎች በመላው ዓለም በሚገኙ 180 የስፖርት ጋዜጠኞች፣ ተንታኞች እና ጸሃፊዎች ነው የሚመረጡት፡፡
6ኛ ሆኖ ለሽልማቱ የታጨውና የአምስት ጊዜ የሽልማቱ አሸናፊ ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በስነ ስርዓቱ አልተገኘም፡፡ የሽልማቱን አዘጋጅ ፍራንስ ፉትቦልንም ተችሏል፡፡