የቀድሞው የጋምቢያ ሚኒስትር በአውሮፖ በአስገድዶ መድፈር ተከሰሱ
ሶንኮ ክሶቹን አስተባብሏል
በቀድሞ የጋምቢያ ፕሬዝደንት ስር ሚኒስትር የነበሩት በአስገድዶ መድፈር እና በሰብአዊነት ላይ በተፈጸመ ወንጀል በሲዊዘርላንድ ተከስሰዋል
የቀድሞው የጋምቢያ ሚኒስትር በአውሮፖ በአስገድዶ መድፈር ተከሰሱ።
ከስልጣን በተወገዱት የቀድሞ የጋምቢያ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ስር ሚኒስትር የነበሩት በአስገድዶ መድፈር እና በሰብአዊነት ላይ በተፈጸመ ወንጀል በሲዊዘርላንድ ተከስሰዋል።
ለበርካታ አስርት አመታት ሲጠበቅ በነበረው በዚህ ክስ፣ የአስገድዶ መድፈር ሰለባዎች ምስክርነታቸውን እንደሚሰጡ ሮይተርስ ዘግቧል።
ቅሬታውን ያቀረበው ትሪያል ኢንተርናሽናል የተባለው የስዊስ አተስተባባሪ ቡድን፣ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የትም ክስ ሊመሰረትባቸው ይችላል ብሏል።
በዚህ ምክንያት የቀድሞው የጋምቢያ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ኦስማን ስንኮ በአውሮፖ የተከሰሱ ከፍተኛ ባለስልጣን ሆነዋል።
ቤሊንዞና በሚገኘው የፊደራል ፍርድ ቤት ችሎቱን ለመስማት ዘጠኝ ከሳሾች ከጋምቢያ እየመጡ መሆናቸው ተገልጿል።
ሶንኮ በተደጋጋሚ ደፍሮናል ከሚሉት ከሳሾች አንዷ የሆነችው ቢንታ ጃምባ ከፍርድ ቤቱ ውጭ ሆና "ጃሜህ እና ተባባሪዎቹ ለፍርድ ይቅረቡ" የሚል መፈክር አሳይታለች።
የስዊዘርላንድ ፍርድ ቤት በሰብአዊነት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ላይ ባቀረበው ክስ የ54 አመቱ ሶንኮ ከ2000-2016 በግድያ፣ በአስገድዶ መድፈር እና በማሰቃየት እና በሌሎች በበርካታ ወንጀሎች ተከሷል።
ሶንኮ ክሶቹን አስተባብሏል።
ማዲ ሴሳይ የተባለችው ሌላኛዋ የአስገድዶ መድፈር ሰለባ እና ከሳሽ "ለረጅም ጊዜ በንዴት እና በአለመረጋጋት ስሜት ውስጥ ሆነን ቆይተናል። አሁን ግን ተስፋ አለኝ፤ ደስተኛም ነኝ። ፍትህ እየሸተተኝ ነው" ስትል ተናግራለች።
የተከሳሽ ጠበቃ ምርመራው ላይ ችግር መኖሩን በመጥቀስ ጉዳዩ ውድቅ እንዲደረግ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
የመብት ተቆርቋሪዎች ዛምቢያን ሲያስተዳድሩ የነበሩት ጃሜህም በሴቶች ላይ ጾታዊ ትንኮሳ በማድረግ ይከሷቸዋል።