የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122 ብር እየገዛ በ125 ብር እየሸጠ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ጎህ ቤቶች ባንክ የትናንቱን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8705 ብር ገዝቶ በ127.3679 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ዳሽን ባንክ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሎ አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ኦሮሚያ ባንክ የህዳር 25 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የአሜሪካ ዶላርን በ124.7099 ብር ገዝቶ በ127.2041 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.6428 ብር ገዝቶ በ127.1357 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
አቢሲኒያ ባንክ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን ምንዛሬ አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ123.8687 ብር እየገዛ በ126.3461 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ገልጿል።