ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ፈጣን የተባለውን ግስጋሴ እያደረገች ዩክሬን ግዛቶች እየተቆጣጠረች ነው ተባለ
ሩሲያ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 235 ካሬ ኪ.ሜ የዩክሬንን መሬት ተቆጣጥራለች ነው የተባለው
ከ2022 ወዲህ ፈጣኑን ግስጋሴ እያደረገ ያለው የሩሲያ ጦር ስትራቴጂክ ከተማ ወደሆነች ኩራኮቭ እየተቃረበ ነው
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የገጠመችው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ፈጣን የተባለውን ግስጋሴ እያደረገች ዩክሬን ግዛቶች እየተቆጣጠረች መሆኑን የዘርፉ ተንታኞች ተናገሩ።
የሩሲያ ጦር ጦርነቱ በፈረንጆቹ 2022 ከጀመረ ወዲህ ከሰሞኑ ሰፊ የዩክሬን መሬትን ተቆጣጥሯል የተባለ ሲሆን፤ በተለይም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ750 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ መሬት መያዙ ተነግሯል።
ሩሲያ በፍጥነት በርካታ ዪክሬን ግዛቶችን መቆጣጠሯ እና አሜሪካ ዩክሬን ሚሳዔሎቿን ተጠቅማ ሞስኮን እንደትመታ መፍቀዷን ተከትሎ ጦርነቱ ወደ ከፋ ደረጃ እየተሸጋገረ መምጣጡንም አንድ አንድ የሩሲያ እና የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
“ሩሲያ የዩክሬን ግዛቶችን በፍጥነት በመቆጣጠር አዲስ የወርሃዊ እና የሳምንታዊ ክብረወሰኖችን እያስመዘገበች ነው” ብሏል ገለልተኛ የሆነው የሩሲያ የዜና ቡድን ኤጀንትስታቮ ባወጣው ሪፖርት።
የሩሲያ ጦር ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 235 ካሬ ኪ.ሜ የዩክሬንን መሬት ተቆጣጥሯል ያለው ቡድኑ፤ ይህም የፈረንጆቹ 2024 አዲስ ክብረወሰን ነው ብሏል።
ሩሲያ እየተገባደደ ባለው የፈረንጆቹ ህዳር ወር ብቻ 600 ካሬ ኪ.ሜ የዩክሬንን መሬት መቆጣጠሯንም ቡድኑ ዲፕ ስቴት የተባለውን እና ለዩክሬን ጦር ቅርበት ያለውን ተቋም ዋቢ በማድረግም መረጃ አጋርቷል።
ሩሲያ ፈጣን ግስጋሴን ማድረግ የጀመረችው ባለፍነው ሐምሌ ወር በምስራቅ ዩክሬን በምትገኘው ኩርስክ ክልል ሲሆን፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሩሲያ ጦር ወደፊት እያደረገ ያለው ግስገገሴ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱም ታውቋል።
አሁን ላይ የሩሲያ ጦር ስትራቴጂክ ከተማ ወደሆነች ኩራኮቭ እየተቃረበ ነው የተባለ ሲሆን፤ ከተማዋ በዶኔስክ ክልል ለምትገኘው ፖክሮቨስክ የሎጂስቲክ ማዕከጀል መሆኗም ይገርላታል።
በዋሽንግተን የሚገኘው የጦርነት ጥናት ተቋም ተንታኞች በሪፖርታቸው “የሩሲያ ኃይሎች በቅርቡ እያደረጉት ያለው ግስጋሴ በፈረንጆቹ 2023 ከነበረው በእጅጉ የሚበልጥ ነው” ብለዋል።
ሩሲያ ምእራባውያን ምንም ይበል ምን በዩክሬን ያያዝኩትን ግብ ከማሳካት የሚያስቆመኝ የለም ብላለች።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው፤ የሩሲያ ጦር የየኩሬንን ግዛት ሙሉ በሙሉ ለቆ መውጣት እስካልቻለ ድረስ ሰላም መስፈን አይችልም ሲሉ ተናግረዋል።
ዩየሩሲያ ክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ያሳለፈነው ሳምንት የነበረው ክስተት ግጭቱ ወደ ከፍተኛ ሁኔታ መሸጋሩ የታየበት ነበር።
ጦርነቱ እንደ አዲስ ያገረሸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዩክሬን የአሜሪካ የረጅም ርቀት ሚሳዔሎችን ተጠቅማ የሩሲያ ግዛት ውስጥ ጥቃት እንደትፈጽም መፍቀዳቸውን ተከትሎ ነው።
ሞስኮ ዩክሬንን በአዲስ የመካከለኛ ርቀት ባሊስቲክ መሳሪያ ስትመታ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ አስደንግጦ ተጨማሪ ስጋትን ከፍ በማድረግ የሩሲያ ዩክሬን የሚዔል ፍጥጫውን ትንሽ ረገብ አድርጎታል።