ዋትስአፕ አዲስ "ፊቸር" አስተዋወቀ
በሜታ ኩባንያ ስር ያለው ግዙፉ ማህበራዊ ሚዲያ ዋትስአፕ የጽምጽ መልእክትን ወደ ጹሁፍ የሚቀይር አዲስ "ፊቸር" ማስተዋወቁ ተገልጿል።
ዋትስአፕ አዲሱ 'ፊቸር' በመላው አለም ለሚገኙ ተጠቃሚዎች በቀጣይ ሳምንታት ይፋ ይሆናል ብሏል
በሜታ ኩባንያ ስር ያለው ግዙፉ ማህበራዊ ሚዲያ ዋትስአፕ የጽምጽ መልእክትን ወደ ጹሁፍ የሚቀይር አዲስ 'ፊቸር' ወይም አገልግሎት ማስተዋወቁ ተገልጿል።
አዲሱ "ፊቸር" በተለይም የጽምጽ መልእክትን ለመስማት አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ግንኙነትን ለማቀላጠፍ እና ሰአት ለመቆጠብ ያስችላል ተብሏል።
ኩባንያው እንደገለጸው ተጠቃሚዎች "ሴቲንግ" ላይ 'ኮንቨርሴሽን' የሚለውን በመጫን "የድምጽ መልእክትን ወደ ጽሁፍ ቀይር" የሚለውን ፊቸር በመምረጥ አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉ። የሚፈልጉተን ቋንቋም ከተመሳሳይ 'ሴክሽን' ወይም ዘርፍ መምረጥ ይችላሉ ብሏል ኩባንያው።
ተጠቃሚዎች 'ፊቸሩን' አክቲቬት ካደረጉ በኋላ የጽምጽ መልእክቱን በመጫን እና ከእዚያም "ወደ ጹሁፍ ቀይር" የሚለውን በመምረጥ መቀየር ይችላሉ።
ነገርግን ኩባንያው እንደገለጸው ምርጫዎቹ ለእያንዳንዱ መልክት አክቲቬት መደረግ የሚጠበቅባቸው በመሆኑ ሁሉንም ወደ ተጠቃሚዎች የሚላኩ የድምጽ መልክቶች ወዲያውኑ ወደ ጽሁፍ አይቀይርም።
ዋትስአፕ አዲሱ 'ፊቸር' በመላው አለም ለሚገኙ ተጠቃሚዎች በቀጣይ ሳምንታት ይፋ ይሆናል ብሏል።
በ(ios) መሳሪያዎች ላይ
አገልግሎት የሚሰጥበት ቋንቋ እንደ ኦፐሬቲንግ ሲስተሙ እና ቨርዥኑ ይለያያል።
ቨርዥኑ ወይም አይነቱ (iOS16) ከሆነ ፊቸሩ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ስፔንኛ፣ ጀርመንኛ፣ ጣሊያንኛ፣ ጃፓንኛ፣ ኮሪያንኛ፣ ፖርቹጋልኛ፣ ሩሲያኛ፣ ቱርክኛ፣ ቻይንኛ እና አረብኛን ጨምሮ በ 13 ቋንቋቸው አገልግሎት ይሰጣል።
(ios17) ከሆነ ደግሞ ዳኒሽ፣ ፊኒሽ፣ ኖርዌጂያን፣ ደች፣ ስዊዲሽ እና ታይ ቋንቋዎችን ይጨምራል።
በአንድሮይድ መሳሪያዎች ላይ
ይህ 'ፊቸር' በአሁኑ ወቅት በእንግሊዝኛ፣ በፖርቹጋልኛ፣ በስፔንኛ እና በሩሲያኛ ቋንቋ ይሰራል።
ዋትስአፕ ይህን ያደረገው ለተጠቃሚዎች ተጨማሪ ምርጫ ለመስጠት እና የድምጽ መልእክት ልውውጥ በቀን ተቀን ግንኙነት ውስጥ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ነው ብሏል።