የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ከአምስት ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ ቅዳሜ ህዳር ህዳር 14 2017 ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ቢያስቀጥልም ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ጸደይ ባንክ የህዳር 20 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ በሳንቲሞች ጭማሪ አድርጎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.4645 ብር ገዝቶ በ126.9538 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ የትናንቱን የምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.4134 ብር ገዝቶ በ126.9017 ብር እየሸጠ ይገኛል።
አቢሲኒያ ባንክ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትንና የሚሸጥበትን እለታዊ ተመን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ123.8647 ብር ገዝቶ በ126.3420 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ነው ባንኩ ያስታወቀው።