ኢኮኖሚ
የነሃሴ 29 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ምን ይመስላል?
ወጋገን ባንክ እስከ መስከረም 30 ድረስ አንድ ዶላርን በ115 ብር እየገዛ በ119 ብር እንደሚሸጥ አስታውቋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ዶላር በ106 ብር እየገዛ በ118 ብር እየሸጠ ነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 29 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ከትናንቱ ጭማሪ ያሳየ የዋጋ ተመንን አውጥቷል።
ባንኩ አንድ ዶላር በ106.3684 ብር ገዝቶ በ118.0689 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው ያስታወቀው።
ወጋገን ባንክ መጪውን አዲስ አመት አስመልክቶ እስከ መስከረም 30 የሚቆይ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
ባንኩ አንድ ዶላር በ115 ብር ገዝቶ በ119 ብር እንደሚሸጥ አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ105.4467 ብር እየተገዛ በ119.1548 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
ዳሽን ባንክም ከትናንቱ የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ ማሻሻያ አድርጎ አንድ ዶላርን በ105.4350 ብር እየገዛ በ118.6144 ብር እየገዛ መሆኑን ነው የገለጸው።