ባንኮች እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመናቸውን ይፋ ሲያደርጉ ከትናንቱ በሳንቲሞች ጭማሪ አድርገዋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 28 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋን ሰሞኑን ሲገዛበት በነበረበት ተመሳሳይ በሆነ ዋጋ በ105.4304 ብር እየገዛ ይገኛል። መሸጫው ላይም ጭማሪ ሳያደርግ በ117.0277 ብር እየሸጠ ይገኛል።
የእንግሊዝ ፓውንድ በ132.5631 ብር እየገዛ በ147.8322 ብር እንደሚሸጥም አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ105.4467 ብር እየተገዛ በ119.1548 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በለቀቀው እለታዊ የውጭ ምንዛሬ የዋጋ ዝርዝር አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113.0300 ብር እየገዛ በ117.0200 ብር እንደሚሸጥ አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.9599 ብር እየገዛ ሲሆን መሸጫው ደግሞ 118.6131 ብር መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን አመላክቷል።
አቢሲኒያ ባንክ ትናንት ያወጣውን እለታዊ የምንዛሬ ተመን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ የአሜሪካ ዶላር በ105.4407 ብር እየገዛ በ118.0936 ብር እየተሸጠ ነው።