በህዳር 21 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ገባ?
የግል ንግድ ባንኮች አንድ ዶላር እስከ 124 ብር ገዝተው እስከ 127 ብር እየሸጡ ይገኛሉ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122 ብር እየገዛ በ125 ብር እየሸጠ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ከአምስት ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ ህዳር ህዳር 14 2017 ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ቢያስቀጥልም ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ123.9920 ብር ገዝቶ በ126.4718 ብር እየሸጠ ይገኛል።
አቢሲኒያ ባንክ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትንና የሚሸጥበትን እለታዊ ተመን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ123.8647 ብር ገዝቶ በ126.3420 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ነው ባንኩ ያስታወቀው።