አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እንዴት ለሰው ልጆች መጥፋት ምክንያት ሊሆን ይችላል?
በርካታ የዓለማችን ኮምፒውተር ጠበብቶች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በስጋትነት መፈረጃቸውን ቀጥለዋል
የተወሰኑ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ቢያንስ ለስድስት ወር ያህል ተጨማሪ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማሻሻያዎች እንዳይኖሩ ጠይቀዋል
የዓለማችን ቴክኖሎጂ በየጊዜው እየዘመነ መጥቶ የሰው ልጆችን ህይወት በማቅለል ላይ ይገኛል።
ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ብዙ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ባንድ ላይ በመያዝ ፍጹም አቅም መፍጠር የቻሉ የአርቲፊሻል ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ይፋ ሆነዋል።
እነዚህ ፈጠራዎች ግን በተለይም የኮምፒውተር ጠበብቶችን ብእጉ እንዳሳሰባቸው ፈጠራው ለራሱ ለሰው ልጆችም አደጋ መሆኑን በመናገር ላይ ናቸው።
ዩሮ ኒውስ የአርቲፊሻል ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች እንዴት ለሰው ልጆች ስጋት ይሆናል ሲል ባለሙያዎችን አነጋግሮ የትንታኔ ይዘቱን አጋርቷል።
የቀድሞው የጎግል ቴክኖሎጂ ባለሙያ የሆኑት ሞ ጋውዳት እንዳሉት ቴክኖሎጀሂው የሰው ልጆችን ህይወት ቀላል በማድረጉ ሰዎች ልጅ እንዳይወልዱ ሊያደርግ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
እንደ ባለሙያው ገለጻ ከሆነ ወላጆች ለልጆቻቸው ስለ አርቲፊሻል ቴክኖሎጂ ማስተማር የለባቸውም፣ ቴክኖሎጂውን ማስተማር የለባቸውም።
የብዙ ቴክኖሎጂዎች ድምር ውጤት የሆነው አርቲፊሻል ቴክኖሎጂ ሁሉም ነገሮችን በቀላሉ በማቅረብ ሰዎች የበለጠ ነገሮችን ለማወቅ ያላቸውን ፍላጎት የሚቀንስ ነውም ብሏል ባለሙያው፡፡
ቴክኖሎጂው የሰው ልጆችን ያለመፈለግ ስሜት በመጨመር ሰዎች ከመተዛዘን ይልቅ ወደ አሉታዊ አመለካከት እና ድርጊቶች እንዲያመሩ የማድረግ እድል አለውም ተብሏል።
ይህን ተከትሎም ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ጅምላ ጨራሽ ወረርሽኞች እና የጦር መሳሪያ እንዲፈበረኩ እንደሚያደርግም ባለሙያው አስጠንቅቀዋል።
የዓለማችን ቀዳሚ ባለጸጋ የሆኑት ኢለን መስክ እና የአፕል መስራቹ ስቲቭ ዋዝኒያክ በይፋ አዲስ የአርቲፊሻል ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ቢያንስ ለስድስት ወራት እንዲታገዱ በፊርማ መጠያቃቸው ይታወሳል።
በአጠቃላይ አርቲፊሻል ቴክኖሎጂ የሰው ልጆችን ስራ በመረከብ፣ አላስፈላጊ ፉክክሮችን በመፍጠር እና የሰው ልጆችን ፈጠራ በመግታት ለሰው ልጆች ስጋት መሆኑን በመናገር ላይ ናቸው።
የቡድን ሰባት ሀገራት ከሁለት ሳምንት በፊት በጃፓኗ ሂሮሽማ ባደረገው ጉባኤ አርቲፊሻል ቴክኖሎጂ የቁጥጥር ስርዓት ሊዘረጋለት እንደሚገባ ከስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል።
በርካታ የዓለማችን ሀገራትም ቻት ጅፒቲን ጨምሮ በርካታ የአርቲፊሻል ቴክኖሎጂ ሰጠራዎችን በሀገራቸው ጥቅም ላይ እንዳይውል ክልከላ በመጣል ላይ ይገኛሉ።
የተወሰኑ ሀገራት ደግሞ ከራሳቸው ህዝብ ሰነ ልቦና እና ፍላጎት ጋር ተስማሚ የሆኑ የአርቲፊሻል ቴክኖሎጂዎችን በማልማት ላይ ናቸው።