“ዳብዋላስ” በቀን 200 ሺህ ምሳዎችን ለደንበኞቻቸው የሚያደርሱት ህንዳውያን
“ዳብዋላስ” የምሳ እቃዎችን ከመኖሪያ ቤቶች ተቀብለው ለደንበኞቻቸው ለማቅረብ ቴክኖሎጂ አይጠቀሙም
በምግብ አቅርቦት 130 ዓመታት ያገለገሉት “ዳብዋላስ” ጋር ስህተት ፈጽሞ አይታሰብም
የቴክኖሎጂ መስፋፋትን ተከትሎ ከቀርብ ጊዜያት ወዲህ የፈለግነውን አይነት ምግብ አዘን ያለንበት ድረስ ማስመጣት እየተለመደ መጥቷል።
በህንዷ ሙንባይ ግን ምግብን ባሉበት የማስመጣት አገለግሎት ከተጀመረ ከ100 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።
ዛሬ “ዳብዋልስ” ስለሚባሉት እና ለ130 ዓመታት ምሳ ከመኖሪያ ቤት በመቀበል በየመስሪያ ቤቶች የማቅረብ አገልግሎት ላይ የተሳተፈ አገልግሎት ሰጪ ድርጅንት ልናስተዋውቃችሁ ወደድን።
በፈረንጆቹ 1980ዎቹ ስራ እንደጀመረ የሚነገርለት ዳብዋላስ የምግብ አቅርቦት ድርጅት በዓለማችን ላይ ስኬታማ ተብሎ ከተቀመጡ የንግድ ስራዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ይገርለታል።
ዳብዋላስ በስራ ላይ ላይ ሰራተኞች ምሳ እቃዎችን ከመኖሪያ ቤታቸው በመቀበል ስራ ቦታ የማድረስ አገልግሎት የሚሰራ ድርጅት ሲሆን፤ በየእለቱም 200 ሺህ ገደማ ምሳ እቃዎችን ለደንበኞቹ የሚያደርስ ድርጅት ነው።
200 ሺህ የምሳ እቃዎችን ከመኖሪያ ቤት ተቀብለው በየመስሪያ ቤቱ ለሚጠብቋቸው ደንበኞቻው ለማድረስም 3 ሰዓታት ብቻ ይፈጅባቸዋል ነው የተባለው።
“ዳብዋላስ” ምሳ እቃዎችን ለመቀበል እና ለማድረስ ጎግል ማፕ፣ ኪው አር ኮድ እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን አይጠቀሙም የተባለ ሲሆን፤ እያንዳንዱን ምሳ እቃ እና መኖሪያ ቤት እንዲሁም የሚያደርሱበትን አድራሻ ለመለየት የቆየ የራሳቸው አሰራር እንዳላቸውም ተነግሯል።
የምሳ እቃዎችን ተቀብለው ወደሚፈለግበት ቦታ ለማድረስም ዳብዋላስ” በብዛት ብስክሌቶችን የሚተቀሙ ሲሆን፤ የባቡር ትራንስፖርትን እንደሚተቀሙም ይነገራል።
“ዳብዋላስ” ጋር ሰዓት ማርፈድ እና ስህተት ፈጽሞ አይታሰብም የተባለ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ በ2010 በተሰራ ጥናት ከደረሱዋቸው በሚሊየን የሚቆጠሩ የምሳ እቃዎች ውስጥ ያጋጠመው ስህተት 34 ብቻ እንደሆነም ተይቷል።